ከዚህ በኋላ የከናዕና ልጅ ሴዴቅያስ ወደ ሚክያስ ቀረብ ብሎ በጥፊ በመምታት “ኧረ ከመቼ ወዲህ ነው የጌታ መንፈስ ከእኔ አልፎ አንተን ያነጋገረህ?” አለው።
ኢዮብ 16:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም አፋቸውን ከፈቱብኝ፥ እያላገጡ ጉንጬን ጠፈጠፉኝ፥ በአንድነትም ተሰበሰቡብኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎች በፌዝ አፋቸውን ከፈቱብኝ፤ በንቀት ጕንጬን ጠፈጠፉኝ፤ በአንድነትም በላዬ ተሰበሰቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎች በዙሪያዬ ተሰብስበው ተዘባበቱብኝ፤ እያፌዙም በጥፊ መቱኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቍጣው ጣለኝ፤ ጥርሶቹንም አፋጨብኝ፤ ፍላጻዎቹንም በእኔ ላይ ፈተነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም አፋቸውን ከፈቱብኝ፥ እያላገጡ ጕንጬን ጠፈጠፉኝ፥ በአንድነትም ተሰበሰቡብኝ። |
ከዚህ በኋላ የከናዕና ልጅ ሴዴቅያስ ወደ ሚክያስ ቀረብ ብሎ በጥፊ በመምታት “ኧረ ከመቼ ወዲህ ነው የጌታ መንፈስ ከእኔ አልፎ አንተን ያነጋገረህ?” አለው።
የክንዓናም ልጅ ሴዴቅያስ ቀረበ፥ ሚክያስንም በጥፊ መታውና እንዲህ አለ፦ “የጌታ መንፈስ ከአንተ ጋር ለመነጋገር በምን ዓይነት መንገድ ከእኔ አለፈ?”
ዔ። ጠላቶችሽ ሁሉ አፋቸውን አላቀቁብሽ፥ እያፍዋጩና ጥርሳቸውን እያፋጩ፦ ውጠናታል፥ ነገር ግን ተስፋ ያደረግናት ቀን ይህች ናት፥ አግኝተናታል አይተናትማል ይላሉ።
አንቺ ግን ቤተልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትንሽ ነሽ፥ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘለዓለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።
በቀባኸው በቅዱሱ ብላቴናህ በኢየሱስ ላይ ሄሮድስና ጴንጤናዊው ጲላጦስ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር፥ እጅህና አሳብህ እንዲሆን አስቀድመው የወሰኑትን ሁሉ ሊፈጽሙ፥ በዚች ከተማ በእውነት ተሰበሰቡ።