ኢዮብ 15:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእግዚአብሔርንስ ምሥጢር ሰምተሃልን? ጥበብን የግልህ ለማድረግ ትመኛለህን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእግዚአብሔር የመማክርት ጉባኤ ላይ ነበርህን? ጥበብስ የተሰጠው ለአንተ ብቻ ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በውኑ የእግዚአብሔርን ምሥጢር ሰምተሃልን? ሰብአዊ ጥበብን ሁሉ የምታውቅ አንተ ብቻ የሆንክ ይመስልሃልን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርንስ ትእዛዝ ሰምተሃልን? ወይስ እግዚአብሔር አማካሪው አድርጎሃልን? ወይስ ጥበብን ለብቻህ አድርገሃልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርንስ ምሥጢር ሰምተሃልን? ወይስ ጥበብን ለብቻህ አድርገሃልን? |
በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ “የሰማያትና የምድር ጌታ አባት ሆይ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ።
ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም፤ ባርያ ጌታው የሚያደርገውን አያውቅምና፤ ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ፤ ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ለእናንተ አስታውቄአችኋለሁና።