ኢዮብ 15:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በደልህ ንግግርህን ይመራዋል፥ የተንኰለኞችንም አንደበት ትመርጣለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኀጢአትህ አፍህን ታስተምረዋለች፤ የተንኰለኞችንም አነጋገር መርጠህ ትይዛለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በደለኛነትህ በአነጋገርህ ይታወቃል፤ ነገር ግን በብልጠት አነጋገር ልትሸፍነው ትሞክራለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአፍህ ንግግር የተነሣ መጠንህ ይታወቃል፥ የኀያላኑንም ቃል አልለየህም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በደልህ አፍህን ያስተምረዋል፥ የተንኰለኞችንም አንደበት ትመርጣለህ። |
መልካም ሰው በልቡ ከሚገኘው መልካም መዝገብ መልካሙን ያወጣል፤ ክፉ ሰውም በልቡ ከሚገኘው ክፉ መዝገብ ክፉውን ያወጣል፤ በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፉ ይናገራልና።