ኢዮብ 15:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተደመሰሱም ከተሞች ውስጥ፥ ሰውም በሌለባቸው፥ ክምር ለመሆን በተመደቡ ቤቶች ውስጥ ተቀምጦአልና አዲሱ መደበኛ ትርጒም መኖሪያው በፈራረሱ ከተሞች፣ የፍርስራሽ ክምር ለመሆን በተቃረቡ፣ ሰው በማይኖርባቸው ወና ቤቶች ውስጥ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ይህ ሰው በወደሙ ከተሞች፥ ሰው በማይኖርባቸውና ለመፍረስ በተቃረቡ ቤቶች ውስጥ ይኖራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተፈቱም ከተሞች ውስጥ ይኖራል፥ ሰውም በሌለባቸው ቤቶች ይገባል፥ እርሱ ያዘጋጀውንም ሌሎች ይወስዱታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በተፈቱም ከተሞች ውስጥ፥ ሰውም በሌለባቸው፥ ክምር ለመሆን በተመደቡ ቤቶች ውስጥ ተቀምጦአልና |
“ሞሬታዊው ሚክያስ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን ትንቢት ተናግሮ ነበር፤ እርሱም ለይሁዳ ሕዝብ ሁሉ፦ ‘የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፥ ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፥ የቤቱም ተራራ እንደ ዱር ከፍታ ይሆናል’ ብሎ ተናገረ።
በደልን ይቅር የሚል፥ የርስቱን ትሩፍ ዓመጽ የሚያሳልፍ እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? ርኅራኄ ይወድዳልና ቁጣውን ለዘለዓለም አያቆይም።