ኢዮብ 15:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በውኑ ጠቢብ ሰው እንደ ነፋስ በሆነ እውቀት ይመልሳልን? ሆዱንስ በምሥራቅ ነፋስ ይሞላልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ጠቢብ ሰው በከንቱ ንግግር መልስ ይሰጣልን? ወይስ በምሥራቅ ነፋስ ሆዱን ይሞላል? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በውኑ ብልኅ ሰው እንደ ነፋስ የማይጨበጥ ነገር ይናገራልን? በሆዱስ ጐጂ የሆነ ሐሳብ ሊኖረው ይገባልን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በውኑ ጠቢብ ሰው እንደ ነፋስ በሆነ ዕውቀት ይመልሳልን? ሆዱንስ በሥቃይ ይሞላልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ ጠቢብ ሰው እንደ ነፋስ በሆነ እውቀት ይመልሳልን? በሆዱስ የምሥራቅን ነፋስ ይሞላልን? |
ኤፍሬም ነፋስን ያሰማራል፥ ቀኑን ሙሉ የምሥራቅን ነፋስ ይከተላል፤ ሐሰትንና ዓመጻን ያበዛል፤ ከአሦር ጋር ቃል ኪዳን ያደርጋሉ፥ ወደ ግብጽም ዘይት ይወስዳሉ።