ኢዮብ 15:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድሪቱ ለእነርሱ ብቻ ተሰጥታለችና፥ በመካከላቸውም እንግዳ አልገባባቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድሪቱ ለአባቶቻቸው ተሰጠች፤ በመካከላቸውም ባዕድ አልተቀመጠም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምድሪቱ ለእነርሱ ብቻ ተሰጥታ ነበር፤ መጻተኞችም በመካከላቸው አልተቀላቀሉባቸውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምድር ለእነርሱ ብቻ ተሰጥታለችና፤ በመካከላቸውም እንግዳ ሕዝብ አልገባባቸውምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመካከላቸውም እንግዳ ያልገባባቸው ጠቢባን ከአባቶቻቸው ተቀብለው የተናገሩትን ያልሸሸጉትንም፥ እገልጥልሃለሁ፥ ስማኝ፥ ያየሁትንም እነግርሃለሁ። |
እኔም በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን የምቀመጥ ጌታ አምላካችሁ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ፥ የዚያን ጊዜም ኢየሩሳሌም የተቀደሰች ትሆናለች፥ እንግዶችም ከእንግዲህ ወዲህ አያልፉባትም።