“መቼም በደል የማይሠራ የለምና ሕዝብህ ኃጢአት በመሥራት አንተን ሲያሳዝኑህ፥ አንተም ተቆጥተህ ጠላቶቻቸው ድል እንዲነሡአቸውና ወደ ሌላ አገር ማርከው እንዲወስዱአቸው በምትፈቅድበት ጊዜ፥ ምንም እንኳ ያ አገር ሩቅ ቢሆን፥
ኢዮብ 15:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከንጹሕ ለመመደብ የሰው ልጅ ምንድነው? ጻድቅስ ለመባል ከሴት የተወለደ ምንድነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ንጹሕ ይሆን ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ጻድቅስ ይሆን ዘንድ፣ ከሴት የተወለደ ምንድን ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሰው ንጹሕ ሊሆን ይችላልን? ሥጋ ለባሽስ ጻድቅ ሊሆን ይችላልን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጹሕ ይሆን ዘንድ ሟች ሰው ማን ነው? ጻድቅስ ይሆን ዘንድ ከሴት የተወለደ ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጹሕ ይሆን ዘንድ ሰው ምንድር ነው? ጻድቅስ ይሆን ዘንድ ከሴት የተወለደ ምንድር ነው? |
“መቼም በደል የማይሠራ የለምና ሕዝብህ ኃጢአት በመሥራት አንተን ሲያሳዝኑህ፥ አንተም ተቆጥተህ ጠላቶቻቸው ድል እንዲነሡአቸውና ወደ ሌላ አገር ማርከው እንዲወስዱአቸው በምትፈቅድበት ጊዜ፥ ምንም እንኳ ያ አገር ሩቅ ቢሆን፥
“ኃጢአት የማይሠራ ሰው የለምና በአንተ ላይ ኃጢአት ቢሠሩ፥ ተቈጥተህም ለጠላት አሳልፈህ ብትሰጣቸው፥ ሩቅም ወይም ቅርብ ወደ ሆነ አገር ቢማርኩአቸው፥