ኢዮብ 12:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተደላድሎ የተቀመጠ ሰው መከራን ይንቃል፥ እግሩን ያዳለጠውንም ለመገፍተር ተዘጋጅቶአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የደላቸው በመከራ ያፌዛሉ፤ እግሩ የተንሸራተተውንም ይገፈትራሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ችግር ባልደረሰበት ሰው ዘንድ የተቸገረን ሰው ችግር ማናናቅ ቀላል ነው። ነገር ግን ሊወድቅ የሚንገዳገደውን ሰው ትገፈትሩታላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ በተወሰነው ዕድሜ በሌሎች እንዲወድቅ፥ ቤቱም በኃጥኣን እንዲፈርስ ተዘጋጅቶአል። ነገር ግን ማንም ክፉ ሆኖ ንጹሕ እንደሚሆን አይመን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተዘልሎ በሚቀመጥ ሰው አሳብ መከራ ይናቃል፥ ነገር ግን እግሩን ሊያድጠው ተዘጋጅቶአል። |
እኔ ደግሞ እንደ እናንተ እናገር ዘንድ ይቻለኝ ነበር፥ ነፍሳችሁ በነፍሴ ፋንታ ቢሆን ኖሮ፥ እኔ በእናንተ ላይ ቃል ማሳካት፥ ራሴንም በእናንተ ላይ መነቅነቅ በተቻለኝ ነበር።
ሳትጨልም እግራችሁም በጨለሙት ተራሮች ላይ ሳትሰናከል፥ በተስፋ የምትጠባበቁትን ብርሃን ለሞት ጥላና ለድቅድቅ ጨልማ ሳይለውጠው፥ ለአምላካችሁ ለጌታ ክብርን ስጡ።