ከታመኑ ሰዎችም ቋንቋን ያርቃል፥ የሽማግሌዎችንም ማስተዋል ይወስድባቸዋል።
የታመኑ መካሪዎችን ቋንቋ ያሳጣል፤ የሽማግሌዎችንም ማስተዋል ይወስዳል።
የታመኑትን ሰዎች ዝም ያሰኛቸዋል፤ ከሽማግሌዎችም አስተዋይነትን ይነሣል።
ከታመኑ ሰዎችም ቋንቋን ይለውጣል፤ የሽማግሌዎችንም ምክር ያውቃል።
ከምድር አሕዛብ አለቆች ዘንድ ማስተዋልን ያስወግዳል፥ መንገድም በሌለበት በረሃ ያቅበዘብዛቸዋል።
ልባቸውም እንዳያስተውል ከልክለኸዋል፥ ስለዚህ ከፍ ከፍ አታደርጋቸውም።
በዕድሜ ያረጁ የግድ ጠቢባን አይደሉም፥ ሽማግሌዎችም የግድ ፍርድን አያስተውሉም።
እግዚአብሔር ጥበብን ነሥቷታልና፥ ማስተዋልንም አላደላትምና።
የጻድቅ ከንፈሮች ብዙ ሰዎችን ይመግባሉ፥ አላዋቂዎች ግን ከማስተዋል ጉድለት የተነሣ ይሞታሉ።
የእውነት ከንፈር ለዘለዓለም ትቆማለች፥ ውሸተኛ ምላስ ግን ለቅጽበት ነው።
ውሸተኛ ከንፈር በጌታ ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ እውነትን የሚያደርጉ ግን በእርሱ ዘንድ የተወደዱ ናቸው።