ኢዮብ 12:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኃይልና ጥበብ በእርሱ ዘንድ ናቸው፥ የሚስተውና የሚያስተው የእርሱ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብርታትና ጥበብ ማድረግ በርሱ ዘንድ ይገኛል፤ አታላዩም ተታላዩም በርሱ እጅ ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ብርቱና ድል አድራጊ ነው፤ የሚታለልም ሆነ የሚያታልል ሁለቱም በእርሱ ሥልጣን ሥር ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀይልና ብርታት በእርሱ ዘንድ ናቸው፤ ዕውቀትና ማስተዋልም ለእርሱ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኃይልና ጥበብ በእርሱ ዘንድ ናቸው፥ የሚስተውና የሚያስተው ለእርሱ ናቸው። |
እርሱ ግን ደግሞ ጠቢብ ነው፥ ክፉንም ነገር ያመጣል፥ ቃሉንም አይመልስም፥ በክፉም አድራጊዎች ቤት ላይ በደልንም በሚሠሩ ረዳት ላይ ይነሣል።
ነቢዩ ቢታለል፥ ቃልንም ቢናገር፥ ያንን ነቢይ ያታለልሁ እኔ ጌታ ነኝ፥ በእርሱም ላይ እጄን እዘረጋለሁ፥ ከሕዝቤ ከእስራኤል መካከልም አጠፋዋለሁ።