ኢዮብ 11:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተስፋም ስላለህ ተማምነህ ትቀመጣለህ፥ በዙሪያህ ትመለከታለህ፥ በደኅንነትም ታርፋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተስፋ ስላለ ተደላድለህ ትቀመጣለህ፤ ዙሪያህን ትመለከታለህ፣ ያለ ሥጋት ታርፋለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተስፋ ስላለህ አንተም በመተማመን ትኖራለህ፤ እግዚአብሔር ስለሚጠብቅህ ያለ ስጋት ዐርፈህ ትኖራለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተስፋህንም ታገኝ ዘንድ ተዘልለህ ትቀመጣለህ፤ ያለ ኀዘንና ጭንቀትም በደኅንነት ትኖራለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተስፋም ስላለህ ተዘልለህ ትቀመጣለህ፥ በዙሪያህ ትመለከታለህ፥ በደኅንነትም ታርፋለህ። |
ለእነርሱም እግዚአብሔር በአሕዛብ ዘንድ ያለው የዚህ ምሥጢር ክብር ባለጠግነት ምን እንደሆነ ሊያሳውቅ ወደደ፤ ምሥጢሩም የክብር ተስፋ የሆነው በእናንተ ያለው ክርስቶስ ነው።