እነርሱም ከመረቡ በላይ ባለው ክብ ስፍራ እንዲቆሙ ተደረገ፤ በእያንዳንዱም ጉልላት ዙሪያ በሁለት ረድፍ የተደረደሩ ሁለት መቶ የሮማን ቅርጾች ነበሩ።
ኤርምያስ 52:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የናሱም ጉልላት በላዩ ነበረ፤ የአንዱም ጉልላት ቁመት አምስት ክንድ ነበረ፥ በጉልላቱም ላይ በዙሪያው ሁሉ ከናስ የተሠሩ መረበብና ሮማኖች ነበሩበት፤ በሁለተኛውም ዓምድ ደግሞ እንደዚህ ያለ ነገርና ሮማኖች ነበሩበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአንዱ ዐምድ ዐናት ላይ ያለው የናስ ጕልላት ቁመት ዐምስት ክንድ ሲሆን፣ ዙሪያውንም ሁሉ የሮማን ቅርጽ ባላቸው የናስ ጌጣጌጦች የተዋበ ነበር፤ ሌላውም ዐምድ የሮማኑን ጌጣጌጥ ጨምሮ ከዚሁ ጋራ ተመሳሳይ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእያንዳንዱም ምሰሶ ጒልላት ከነሐስ የተሠራ ሆኖ ሁለት ሜትር ያኽል ከፍታ የነበረውና በመረብና በሮማን ፍሬ ቅርጽ የተጌጠ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የናሱም ጕልላት በላዩ ነበረ፤ የአንዱም ጕልላት ቁመት አምስት ክንድ ነበረ፤ በጕልላቱም ላይ በዙሪያው ሁሉ ከናስ የተሠሩ መርበብና ሮማኖች ነበሩበት፤ በሁለተኛውም ዐምድ ደግሞ እንደዚህ ያለ ነገርና ሮማኖች ነበሩበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የናሱም ጕልላት በላዩ ነበረ፥ የአንዱም ጉልላት ቁመት አምስት ክንድ ነበረ፥ በጕልላቱም ላይ በዙሪያው ሁሉ ከናስ የተሠሩ መረበብና ሮማኖች ነበሩበት፥ በሁለተኛውም ዓምድ ደግሞ እንደዚህ ያለ ነገርና ሮማኖች ነበሩበት። |
እነርሱም ከመረቡ በላይ ባለው ክብ ስፍራ እንዲቆሙ ተደረገ፤ በእያንዳንዱም ጉልላት ዙሪያ በሁለት ረድፍ የተደረደሩ ሁለት መቶ የሮማን ቅርጾች ነበሩ።
በእያንዳንዱ ጉልላት ላይ በመረብ አምሳል የተሠሩት ሰንሰለቶች፥ በእያንዳንዱ ጉልላት ቅርጽ ላይ በሁለት ረድፍ አንዳንድ መቶ ዙር የሆኑ፥ ከነሐስ የተሠሩ አራት መቶ የሮማን ቅርጾች።
አንዱ ዐምድ ስምንት ሜትር ነበረው፤ ጉልላቱ ከነሐስ የተሠራ ነበር፤ የጉልላቱም ቁመት አንድ ሜትር ከሠላሳ ሳንቲ ሜትር ነበር፤ በዙሪያውም ከነሐስ በተሠራ መረብ ላይ የሮማን ፍሬ ቅርጽ የመሰለ ፈርጠኛ ጌጥ ተሠርቶበት ነበር።