ኤርምያስ 51:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሕዛብን የሚዶንንም ነገሥታት ገዢዎችዋንም ሹማምንቶችዋንም ሁሉ የግዛትዋንም ምድር ሁሉ በእርሷ ላይ ለጦርነት አዘጋጁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሜዶንን ነገሥታት፣ ገዦቿንና ባለሥልጣኖቿን ሁሉ፣ በግዛታቸው ሥር ያሉትን አገሮች ሁሉ፣ እነዚህን ሕዝቦች ለጦርነት አዘጋጁባት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባቢሎንን ይወጉ ዘንድ ሕዝቦችን አዘጋጁ፤ መድቡ፤ ወደ ሜዶን ነገሥታት፥ ወደ መሪዎቻቸውና ጦር አዛዦቻቸው እንዲሁም እነርሱ በሚቈጣጠሩአቸው አገሮች ወደሚኖሩ ሠራዊት ሁሉ መልእክት ላኩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሕዛብንም፥ የሜዶንንም ነገሥታት፥ አለቆችንም፥ መሳፍንትንም ሁሉ፥ የግዛታቸውንም ምድር ሁሉ ለዩባት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሕዛብን የሚዶንንም ነገሥታት አለቆችንም ሹማምቶችንም ሁሉ የግዛታቸውንም ምድር ሁሉ አዘጋጁባት። |
ፍላጾችን ሳሉ ጋሻዎችንም አንሡ፤ ጌታ ሊያጠፋት አሳቡ በባቢሎን ላይ ነውና የሜዶንን ነገሥታት መንፈስ አስነሥቶአል፤ የጌታ በቀል ስለ መቅደሱ ሲል የሚበቀለው በቀል በእርሷ ላይ ነውና።
በምድር ላይ ዓላማን አንሡ በአሕዛብም መካከል መለከት ንፉ፥ አሕዛብንም ለጦርነት በእርሷ ላይ አዘጋጁ፤ የአራራትንና የሚኒን የአስከናዝንም መንግሥታት ጥሩባት አለቃንም በእርሷ ላይ ሹሙ፤ እንደ ጠጉራም ኩብኩባ ፈረሶችን በእርሷ ላይ አውጡ።