እናንተንም የሚወጉዋችሁን የከለዳውያንን ሠራዊት ሁሉ ድል ብታደርጉ እንኳ ከእነርሱም መካከል የቆሰሉ ሰዎች ብቻ ቢቀሩ፥ እነርሱም ሁሉ ከየድንኳኖቻቸው ይነሣሉ ይህችንም ከተማ በእሳት ያቃጥላታል።’ ”
ኤርምያስ 50:45 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ጌታ በባቢሎን ላይ የመከረባትን ምክር፥ በከለዳውያንም ምድር ላይ ያሰባትን አሳብ ስሙ፤ በእውነት የመንጋው ትንንሾች እንኳ ይጐትቷቸዋል፤ በእውነት የማደሪያውም በረት በእነርሱ ላይ ይሣቀቃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እግዚአብሔር በባቢሎን ላይ ያቀደውን፣ በባቢሎናውያንም ምድር ላይ ያሰበውን ሐሳብ ስሙ፤ ከመንጋው ታናናሹ ተጐትቶ ይወሰዳል፤ በእነርሱም ምክንያት መሰማሪያቸውን ፈጽሞ ያጠፋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሁን እንግዲህ እግዚአብሔር በባቢሎናውያን ላይ የመከረውን ምክርና በከለዳውያን ምድር ላይ ያቀደውን ዕቅድ ስሙ፤ ልጆቻቸው እንኳ እንደ በግ ግልገሎች ተጐትተው ይወሰዳሉ፤ በእነርሱም ምክንያት መሰማሪያቸው አስደንጋጭ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ እግዚአብሔር በባቢሎን ላይ የመከረባትን ምክር፥ በከለዳውያንም ምድር ላይ ያሰባትን ዐሳብ ስሙ፤ በእውነት የበጎቻቸቸው ጠቦቶች ይጠፋሉ፤ በእውነት ማደሪያዎቻቸውም ባድማ ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ እግዚአብሔር በባቢሎን ላይ የመከረባትን ምክር፥ በከለዳውያንም ምድር ላይ ያሰባትን አሳብ ስሙ፥ በእውነት የመንጋ ትንንሾች ይጎተታሉ፥ በእውነት ማደሪያቸውን ባድማ ያደርግባቸዋል። |
እናንተንም የሚወጉዋችሁን የከለዳውያንን ሠራዊት ሁሉ ድል ብታደርጉ እንኳ ከእነርሱም መካከል የቆሰሉ ሰዎች ብቻ ቢቀሩ፥ እነርሱም ሁሉ ከየድንኳኖቻቸው ይነሣሉ ይህችንም ከተማ በእሳት ያቃጥላታል።’ ”
ስለዚህ ጌታ በኤዶምያስ ላይ የመከረባትን ምክር፥ በቴማንም በሚኖሩ ሰዎች ላይ ያሰባትን አሳብ ስሙ፤ በእውነት የመንጋው ትንንሾች እንኳ ይጐትቷቸዋል፤ በእውነት የማደሪያቸውም በረት በእነርሱ ላይ ይሣቀቃል።