ኤርምያስ 50:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትዕቢተኛው ተሰናክሎ ወድቆአ የሚያነሣውም ማንም የለም፤ በከተሞቹም ውስጥ እሳት አነድዳለሁ፥ በዙሪያውም ያለውን ሁሉ ትበላለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ትዕቢተኛው ይሰናከላል፤ ይወድቃልም፤ የሚያነሣውም የለም፤ በዙሪያው ያሉትን ሁሉ የሚበላ እሳት፣ በከተሞቹ ውስጥ አስነሣለሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንቺ ትዕቢተኛይቱ ተሰናክለሽ ትወድቂአለሽ፤ ደግፎ የሚያነሣሽም አይኖርም፤ ከተሞችሽን በእሳት አቃጥላለሁ፤ በዙሪያሽም ያለው ነገር ሁሉ ይደመሰሳል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንቺ ትዕቢተኛ ሆይ!፥ ትደክሚያለሽ፤ ትወድቂያለሽም፤ የሚያነሳሽም የለም፤ በዛፎችሽ ውስጥ እሳትን አነድዳለሁ፤ በዙሪያሽ ያለውንም ሁሉ ትበላለች።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትዕቢተኛው ተሰናክሎ ይወድቃል የሚያነሣውም የለም፥ በከተሞቹም ውስጥ እሳት አነድዳለሁ፥ በዙሪያውም ያለውን ሁሉ ትበላለች። |
አንተም እንዲህ በል፦ ‘እኔ ከማመጣባት ክፉ ነገር የተነሣ እንዲሁ ባቢሎን ትሰጥማለች አትነሣምም።’ ” የኤርምያስ ቃላት እስከዚህ ድረስ ነው።
ስለዚህም ሞትና ኀዘን፥ ራብም የሆኑት መቅሰፍቶችዋ በአንድ ቀን ይመጣሉ፤ በእሳትም ትቃጠላለች፤ የሚፈርድባት ጌታ እግዚአብሔር ብርቱ ነውና።”