ኤርምያስ 50:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዘሪውንና በመከር ጊዜ ማጭድ የሚይዘውን ከባቢሎን አጥፉ፤ የአስጨናቂው ሰው ከሆነው ሰይፍ ፊት እያንዳንዱ ወደ ወገኑ ይመለሳል እያንዳንዱም ወደ አገሩ ይሸሻል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከባቢሎን ዘር የሚዘራውን፣ በመከር ጊዜ ማጭድ የጨበጠውንም ዐጫጅ አጥፉት፤ ከአጥፊው ሰይፍ የተነሣ፣ እያንዳንዱ ወደ ገዛ ሕዝቡ ይመለስ፤ ወደ ገዛ ምድሩም ይሽሽ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዘሪውንና መከር ሰብሳቢውን ከባቢሎን አስወግዱ፤ በዚያች አገር የሚኖር እያንዳንዱ የውጪ ዜጋ አደጋ የሚጥልባትን ሠራዊት በመፍራት ወደ ወገኑ ይመለሳል፤ ወደ አገሩም ይሸሻል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዘሪውንና በመከር ጊዜ ማጭድ የሚይዘውን ከባቢሎን አጥፉ፤ ከአረማዊው ሰይፍ ፊት የተነሣ እያንዳንዱ ወደ ወገኑ ይመለሳል፤ እያንዳንዱም ወደ ሀገሩ ይሸሻል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዘሪውንና በመከር ጊዜ ማጭድ የሚይዘውን ከባቢሎን አጥፉ፥ ከሚያስጨንቅ ሰይፍ ፊት እያንዳንዱ ወደ ወገኑ ይመለሳል እያንዳንዱም ወደ አገሩ ይሸሻል። |
እርሱም ብዙዎችን አሰነካከለ፥ እርሱም ደግሞ ወደቀ፤ እርስ በርሳቸውም፦ ተነሡ፥ የአስጨናቂው ሰው ከሆነው ሰይፍ ፊት ወደ ወገናችን ወደ ተወለድንባትም ምድር እንመለስ ተባባሉ።
ባቢሎንን ልንፈውሳት ሞከርን፥ እርሷ ግን አልተፈወሰችም፤ ፍርድዋ እስከ ሰማይ ደርሶአልና፥ እስከ ደመናም ድረስ ከፍ ከፍ ብሏልና ትታችኋት እያንዳንዳችን ወደ አገራችን እንሂድ።
ስለዚህ ጌታ፥ የሠራዊት አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ “በየአደባባዩ ሁሉ ላይ ዋይታ ይሆናል፤ በየመንገዱም ሁሉ ላይ ‘ወዮ! ወዮ!’ ይላሉ፤ ገበሬዎቹም ወደ ልቅሶ፥ አልቃሾቹም ወደ ዋይታ ይጠራሉ።