La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 5:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እኔም፦ “የጌታን መንገድና የአምላካቸውን ሕግ አላወቁምና እነዚህ ተሞኝተው ይህን አድርገዋል በእውነት ድሆች ናቸው፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እኔም በልቤ እንዲህ አልሁ፤ “እነዚህ ድኾች ናቸው፤ ሞኞች ናቸው፤ የእግዚአብሔርን መንገድ፣ የአምላካቸውን ሕግ አላወቁምና።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህ በኋላ እኔ እንደዚህ አልኩ፥ “የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ሕግ ስላላወቁ፤ እነዚህ ድኾችና ማስተዋል የጐደላቸው ሰነፎች ናቸው፤ መንገዱንም አይከተሉም።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እኔም እን​ዲህ አልሁ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገ​ድና የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውን ፍርድ አላ​ወ​ቁ​ምና እነ​ዚህ በእ​ው​ነት ድሆ​ችና ደካ​ሞች ናቸው፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እኔም፦ የእግዚአብሔርን መንገድና የአምላካቸውን ሕግ አላወቁምና እነዚህ በእውነት ድሆችና ሰነፎች ናቸው፥

Ver Capítulo



ኤርምያስ 5:4
11 Referencias Cruzadas  

ጫፎችዋ በደረቁ ጊዜ ይሰበራሉ፥ ሴቶችም መጥተው ያቃጥሉአቸዋል፤ የማያስተውል ሕዝብ ነውና ፈጣሪው አይራራለትም፤ ሠሪውም ምሕረት አያደርግለትም።


ደግሞም መጽሐፉን ማንበብን ለማያውቅ፦ “ይህን አንብብ” ብለው በሰጡት ጊዜ እርሱ፦ “ማንበብ አላውቅም” ይላቸዋል።


በአንድ ጊዜ ቂላ ቂሎችና ሞኞች ሆነዋል፤ ጣዖታት የሚያስተምሩት ከግዑዝ እንጨት የማይሻልን ነገር ብቻ ነው።


“ሕዝቤ ሰንፈዋልና አላወቁኝም፤ ሰነፎች ልጆች ናቸው፥ ማስተዋልም የላቸውም፤ ክፉ ነገርን ለማድረግ ብልሃተኞች ናቸው፥ በጎ ነገርን ማድረግ ግን አያውቁም።”


“እነሆ፥ በማይረባ በሐሰት ቃላት ታምናችኋል።


እንዲሁም ሽመላ በሰማይ ጊዜዋን አውቃለች፤ ዋኖስና ጨረባ ዋልያም የመምጫቸውን ጊዜ ይጠብቃሉ፤ ሕዝቤ ግን የጌታን ፍርድ አላወቁም።


ምላሳቸውን ስለ ሐሰት እንደ ቀስት ገተሩ፤ በምድር በረቱ ነገር ግን ለእውነት አይደለም፤ ከክፋት ወደ ክፋት ይሄዳሉና፥ እኔንም አላወቁምና፥ ይላል ጌታ።


ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤ አንተም እውቀትን ትተሃልና ለእኔ ካህን እንዳትሆን ትቼሃለሁ፤ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ።


ዕውሮች ያያሉ፤ አንካሶች ይራመዳሉ፤ ለምጻሞችም ይነጻሉ፤ ደንቆሮዎች ይሰማሉ፤ ሙታን ይነሣሉ፤ ለድሆችም ወንጌል ይሰበካል፤