La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 49:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እናንተ በአሦር የምትኖሩ ሆይ! የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ተማክሮባችኋልና፥ አሳብም አስቦባችኋልና ሽሹ ወደ ሩቅም ስፍራ ሂዱ በጥልቁም ውስጥ ተቀመጡ፥ ይላል ጌታ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“በሐጾር የምትኖሩ ሆይ፣ በጥድፊያ ሽሹ፤ በጥልቅ ጕድጓድ ተሸሸጉ፤” ይላል እግዚአብሔር፤ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በእናንተ ላይ ጠንክሯልና፣ ወረራም ዶልቶባችኋል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የሐጾር ነዋሪዎች እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በእናንተ ላይ ስለ መከረባችሁና ክፉ ዕቅድ ስላቀደባችሁ ርቃችሁ ሽሹ፤ በጥልቁም ዋሻ ተደበቁ።”

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እና​ንተ በአ​ሦር የም​ት​ኖሩ ሆይ! የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ተማ​ክ​ሮ​ባ​ች​ኋ​ልና፥ ክፉ አሳ​ብ​ንም አስ​ቦ​ባ​ች​ኋ​ልና ሽሹ፤ ወደ ሩቅም ሂዱ፤ በጥ​ልቅ ጕድ​ጓ​ድም ውስጥ ተቀ​መጡ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እናንተ በአሶር የምትኖሩ ሆይ፥ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ተማክሮባችኋልና፥ አሳብም አስቦባችኋልና ሽሹ ወደ ሩቅም ሂዱ በጥልቅም ውስጥ ተቀመጡ፥ ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 49:30
4 Referencias Cruzadas  

እርሱ ግን እንዲህ አላሰበም፤ በልቡም ይህ አልነበረም፤ ነገር ግን ዕቅዱ ለማጥፋት፤ ብዙ ሕዝቦችንም ለመደምሰስ ነበር።


እነሆ፥ የሰሜንን ወገኖች ሁሉ እልካለሁ ይላል ጌታ፥ ባርያዬንም የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እወስዳለሁ፥ በዚህችም ምድር በሚቀመጡባትም ሰዎች፥ በዙሪያዋም ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ፤ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፥ ለመሣቀቂያና ለማፍዋጫም ለዘለዓለምም ባድማ አደርጋቸዋለሁ።


አሁንም እነዚህን ምድሮች ሁሉ ለባርያዬ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እጅ አሳልፌ ሰጥቻለሁ፤ እንዲያገለግሉትም የምድረ በዳን አራዊት ደግሞ ሰጥቼዋለሁ።