ኤርምያስ 48:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቂርዮት፥ በባሶራ፥ በሞዓብም ምድር በቅርብና በሩቅ ባሉ ከተሞች ሁሉ ላይ መጥቷል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በቂርዮትና በባሶራ ላይ፤ በሩቅና በቅርብ ባሉት በሞዓብ ከተሞች ሁሉ ላይ መጥቷል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቂርዮት፥ በቦሶራ፥ በሞአብም ምድር ከተሞች ሁሉ ቅርብና ሩቅ በሆኑ ላይ ፍርድ መጥቶአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቤትምዖን ላይ፥ በቂርዮት፥ በባሶራ፥ በሞዓብም ምድር ከተሞች ሁሉ ቅርብና ሩቅ በሆኑ ላይ ፍርድ መጥቶአል። |
ይህ ከኤዶምያስ፥ ልብሱም የቀላ ከባሶራ የሚመጣ፥ አለባበሱ ያማረ፥ በጉልበቱ ጽናት የሚራመድ ማን ነው? “በጽድቅ የምናገር ለማዳንም የምበረታ እኔ ነኝ።”
ከተሞቹም ለሮቤል ነገድ በምድረ በዳ በደልዳላ ስፍራ ያለ ቤጼር፥ ለጋድም ነገድ በገለዓድ ያለ ራሞት፥ ለምናሴም ነገድ በባሳን ያለ ጎላን ነበሩ።