ኤርምያስ 44:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቃሎቼም በእናንተ ላይ ለክፋት በእርግጥ እንደሚጸኑ እንድታውቁ በዚህች ስፍራ እቀጣችኋለሁ፤ ይህም ለእናንተ ምልክት ይሆናል፥ ይላል ጌታ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘በእናንተ ላይ አመጣለሁ ያልሁትን ክፉ ነገር እንደሚፈጸም ታውቁ ዘንድ በዚህ ስፍራ እንደምቀጣችሁ ይህ ምልክት ይሁናችሁ’ ይላል እግዚአብሔር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ቦታ በምቀጣችሁ ጊዜ ‘በእናንተ ላይ ጥፋትን አመጣለሁ’ ብዬ የተናገርኩት ቃል እውነት እንደሚሆን እኔ እግዚአብሔር አረጋግጥላችኋለሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ቃሌም በላያችሁ ለክፋት እንዲጸና ታውቁ ዘንድ በዚች ስፍራ በክፉ እንደምጐበኛችሁ ምልክታችሁ ይህ ነው፥” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቃሌም በላያችሁ ለክፋት እንዲጸና ታውቁ ዘንድ በዚህች ስፍራ እንድቀጣችሁ ምልክታችሁ ይህ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር። |
እርሱ ግን ደግሞ ጠቢብ ነው፥ ክፉንም ነገር ያመጣል፥ ቃሉንም አይመልስም፥ በክፉም አድራጊዎች ቤት ላይ በደልንም በሚሠሩ ረዳት ላይ ይነሣል።
ጌታ እንዲህ ይላል፦ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን ጠላቱ ለሆነው ነፍሱንም ለሚሻው ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እጅ አሳልፌ እንደ ሰጠሁ፥ እንዲሁ፥ እነሆ፥ የግብጹን ንጉሥ ፈርዖን ሖፍራን ለጠላቶቹ ነፍሱንም ለሚሽዋት እጅ አሳልፌ እሰጠዋለሁ።”
ነገር ግን ለአገልጋዮቼ ለነቢያት ያዘዝኳቸው ቃሎቼና ሥርዓቴ በአባቶቻችሁ ላይ አልደረሱምን? ከዚያ እነርሱም ተጸጽተው፦ “የሠራዊት ጌታ በመንገዳችንና በሥራችን መጠን ሊያደርግብን ያሰበውን እንዲሁ አድርጎብናል” በማለት ተቀበሉ።