እነርሱንም የጽሩያ ልጅ ኢዮአብና የዳዊት ሰዎች ወጥተው በገባዖን ኲሬ አጠገብ ተገናቿቸው፤ አንዱ ወገን በኲሬው ወዲህ ማዶ፥ ሌላው ወገን ደግሞ በኲሬው ወዲያ ማዶ ተቀመጠ።
ኤርምያስ 41:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰዎቻቸውንም ሁሉ ይዘው ከናታንያ ልጅ ከእስማኤል ጋር ለመዋጋት ሄዱ፤ በገባዖንም ባለው ታላቅ ኲሬ አጠገብ አገኙት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የናታንያን ልጅ እስማኤልን ሊወጉ ሰዎቻቸውን ሁሉ ይዘው ሄዱ፤ በገባዖንም ባለው በታላቁ ኵሬ አጠገብ ደረሱበት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ከሰዎቻቸው ሁሉ ጋር አሳደው ገባዖን ውስጥ ባለው ታላቅ ኲሬ አጠገብ ደረሱበት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሠራዊቱንም ሁሉ ይዘው ከናታንያ ልጅ ከእስማኤል ጋር ሊዋጉ ሄዱ። በገባዖንም ባለው በብዙ ውኃ አጠገብ አገኙት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰዎቹን ሁሉ ይዘው ከናታንያ ልጅ ከእስማኤል ጋር ሊዋጉ ሄዱ፥ በገባዖንም ባለው በታላቁ ውኃ አጠገብ አገኙት። |
እነርሱንም የጽሩያ ልጅ ኢዮአብና የዳዊት ሰዎች ወጥተው በገባዖን ኲሬ አጠገብ ተገናቿቸው፤ አንዱ ወገን በኲሬው ወዲህ ማዶ፥ ሌላው ወገን ደግሞ በኲሬው ወዲያ ማዶ ተቀመጠ።