ኤርምያስ 4:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አየሁ፥ እነሆም፥ ፍሬያማው እርሻ ምድረ በዳ ሆኖ፥ ከተሞችም ሁሉ ከጌታ ፊት ከጽኑ ቁጣው የተነሣ ፈርሰው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተመለከትሁ፤ እነሆም፣ ፍሬያማው ምድር በረሓ ሆነ፤ ከተሞቹ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት፣ ከብርቱ ቍጣው የተነሣ ፈራረሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለምለሚቱ ምድር ወደ በረሓነት ተለውጣለች፤ ከእግዚአብሔር ብርቱ ቊጣ የተነሣ፥ ከተሞችዋ ሁሉ ፈራርሰዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተመለከትሁ፤ እነሆም ቀርሜሎስ ምድረ በዳ ሆነች፤ ከተሞችም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፊት የተነሣ በእሳት ተቃጠሉ፤ ከጽኑ ቍጣውም የተነሣ ፈጽመው ጠፉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አየሁ፥ እነሆም፥ ፍሬያማ እርሻ ምድረ በዳ ሆነች፥ ከተሞችም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፊት ከጽኑ ቍጣው የተነሣ ፈርሰው ነበር። |
ምድሪቱ የምታለቅሰው፥ የአገሩ እጽዋት ሁሉ የሚደርቀው እስከ መቼ ነው? የተቀመጡባት ሰዎች፦ “ፍጻሜያችንን አያይም” ብለዋልና ስለ ክፋታቸው እንስሶችና ወፎች ተጠራርገው ጠፍተዋል።
ምድሪቱም ባድማ ትሆናለችና ከይሁዳ ከተሞችና ከኢየሩሳሌም አደባባይ የእልልታን ድምፅና የደስታን ድምፅ፥ የሙሽራውን ድምፅና የሙሽራይቱን ድምፅ አጠፋለሁ።
“ለተራሮች ልቅሶንና እንጉርጉሮን ለምድረ በዳ ማሰማርያዎችም ዋይታን አነሣለሁ፥ ሰው እንዳያልፍባቸው ባድማ ሆነዋልና። ሰዎችም የከብቱን ድምፅ አይሰሙም፤ ከሰማይ ወፎች ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ሸሽተው ሄደዋል።
ዛይ። ጌታ መሠዊያውን ጣለ፥ መቅደሱን ጠላ፥ የአዳራሾችዋንም ቅጥር በጠላት እጅ አሳልፎ ሰጠ፥ ድምፃቸውን እንደ ዓመት በዓል ቀን በእግዚአብሔር ቤት ከፍ ከፍ አደረጉ።
በጌታ የመዓት ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤ ምድር ሁሉ በቅንዓቱ እሳት ትበላለች፥ እርሱም በምድር የሚኖሩትን ሁሉ አስፈሪ ፍፃሜ ያመጣባቸዋልና።