La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 37:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የጌታም ቃል ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፦

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህ በኋላ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለሴዴቅያስ በመልእክተኞቹ አማካይነት እንዲህ ብዬ እንድነግረው አዘዘኝ፦ “እነሆ አንተን ለመርዳት መጥቶ የነበረው የግብጽ ሠራዊት ወደ አገሩ ወደ ግብጽ በመመለስ ላይ ነው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ ነቢዩ ወደ ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ ሲል መጣ፦

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፦

Ver Capítulo



ኤርምያስ 37:6
4 Referencias Cruzadas  

እነሆ፥ አፈር ደልድለው የመሸጉ፥ ከተማይቱን ሊይዙአት ቀርበዋል፤ ከሰይፍና ከራብ ከቸነፈርም የተነሣ ከተማይቱ ለሚዋጉአት ለከለዳውያን እጅ ተሰጥታለች፤ የተናገርኸውም ሆኖአል፥ እነሆም፥ አንተ ታየዋለህ።


የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ እንዲህ ብሎ አሳስሮት ነበርና፦ “ስለምን እንዲህ ብለህ ትንቢት ትናገራለህ፦ ‘ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ይህችን ከተማ ለባቢሎን ንጉሥ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ እርሱም ይይዛታል፤


የፈርዖንም ሠራዊት ከግብጽ ወጣ፤ ኢየሩሳሌምንም ከብበዋት የነበሩ ከለዳውያን ይህን ወሬ በሰሙ ጊዜ ከኢየሩሳሌም ተመለሱ።


“የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ እኔን እንድትጠይቁኝ የላካችሁን የይሁዳን ንጉሥ እንዲህ በሉት፦ ‘እነሆ፥ ሊረዳችሁ የወጣው የፈርዖን ሠራዊት ወደ አገሩ ወደ ግብጽ ይመለሳል።