ኤርምያስ 37:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤርምያስም ደግሞ ንጉሡን ሴዴቅያስን እንዲህ አለው፦ “በእስር ቤት የጣላችሁኝ አንተን ወይስ ባርያዎችህን ወይስ ይህን ሕዝብ ምን በድያችሁ ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤርምያስም ንጉሡ ሴዴቅያስን እንዲህ አለው፤ “በግዞት ቤት ያሰራችሁኝ በአንተና በመኳንንትህ ወይም በዚህ ሕዝብ ላይ ምን ወንጀል ፈጽሜ ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በኋላ እንዲህ ብዬ ጠየቅሁት፦ “እስር ቤት ታስገባኝ ዘንድ በአንተ፥ በመኳንንትህና በዚህ ሕዝብ ላይ የፈጸምኩት ወንጀል ምንድነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤርምያስም ደግሞ ንጉሡን ሴዴቅያስን እንዲህ አለው፥ “በግዞት ቤት የጣላችሁኝ አንተን፥ ወይስ አገልጋዮችህን፥ ወይስ ሕዝብህን ምን በድያችሁ ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤርምያስም ደግሞ ንጉሡን ሴዴቅያስን እንዲህ አለው፦ በግዞት ቤት የጣላችሁኝ አንተን ወይስ ባሪያዎችህን ወይስ ሕዝብህን ምን በድያችሁ ነው? |
በውኑ የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስና ሕዝቡ ሁሉ ገደሉትን? በውኑ ንጉሡ ጌታን አልፈራን? ወደ ጌታስ አልተማጠነምን? ጌታስ በእነርሱ ላይ የተናገረውን ክፉ ነገር አልተወምን? እኛም በነፍሳችን ላይ ታላቅ ክፋት እናደርጋለን።”
ጳውሎስም ሸንጎውን ትኩር ብሎ ተመልክቶ “ወንድሞች ሆይ! እኔ እስከዚች ቀን ድረስ በመልካም ሕሊና ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ኖሬአለሁ፤” አለ።
እንግዲህ በድዬ ወይም ሞት የሚገባውን ነገር አድርጌ እንደሆነ ከሞት ልዳን አልልም፤ እነዚህ የሚከሱኝ ክስ ከንቱ እንደሆነ ግን ለእነርሱ አሳልፎ ይሰጠኝ ዘንድ ማንም አይችልም፤ ወደ ቄሣር ይግባኝ ብዬአለሁ፤” አለ።