ኤርምያስ 37:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤርምያስም በጉድጓድ ውስጥ ለውኃ ማከማቻ ወደሚሆን ቤት ወደ ጓዳዎቹ ገባ፤ እርሱም በዚያ ብዙ ቀን ከተቀመጠ በኋላ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤርምያስም በጕድጓድ ውስጥ እንዲቀመጥ ተደረገ፤ በዚያም ረዥም ጊዜ ቈየ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም ምድር ቤት ውስጥ በሚገኝ ክፍል ለብዙ ጊዜ ቈየሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤርምያስም ወደ ጕድጓድ ቤት ወደ ጓዳዎቹ ገባ፤ ኤርምያስም በዚያ ብዙ ቀን ተቀመጠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤርምያስም ወደ ጕድጓድ ቤት ወደ ጓዳዎቹ ገባ፥ ኤርምያስም በዚያ ብዙ ቀን ከተቀመጠ በኋላ፥ |
ኤርምያስንም ወሰዱት፤ በእስር ቤቱም አደባባይ ወደነበረው ወደ ንጉሡ ልጅ ወደ መልክያ ጉድጓድ ውስጥ ኤርምያስን በገመድ አውርደው ጣሉት። በጉድጓድም ውስጥ ጭቃ እንጂ ውኃ አልነበረበትም፤ ኤርምያስም ወደ ጭቃው ውስጥ ገባ።