ጌታ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ሁለት የድንጋይ ጽላቶች እንደ ፊተኞቹ አድርገህ ጥረብ፥ በሰበርኻቸው በፊተኞቹ ጽላቶች የነበሩትን ቃሎች እጽፍባቸዋለሁ።
ኤርምያስ 36:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤርምያስም ሌላ ክርታስ ወሰደ፥ ለኔርያም ልጅ ለጸሐፊው ለባሮክ ሰጠው፤ እርሱም የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአቄም በእሳት ያቃጠለውን የመጽሐፉን ቃላት ሁሉ ኤርምያስ እየነገረው ጻፈበት፥ ደግሞም እንደ ቀድሞው ያለ ተመሳሳይ ብዙ ቃላት ተጨመረበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤርምያስም ሌላ ብራና ወስዶ ለኔርያ ልጅ ለጸሓፊው ለባሮክ ሰጠው፤ ባሮክም የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአቄም በእሳት ባቃጠለው ብራና ላይ የነበረውን ቃል ሁሉ ከኤርምያስ አፍ ተቀብሎ ጻፈበት፤ ብዙ ተመሳሳይ ቃልም ተጨመረበት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሌላ የብራና ጥቅል ወስጄ ለጸሐፊዬ ለባሮክ ሰጠሁት፤ እርሱም በቃል የነገርኩትን ሁሉ ጻፈበት፤ በዚህ ዐይነት የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአቄም ባቃጠለው ብራና ተጽፎ የነበረውን ጻፈ፤ ሌሎችም ብዙ ተመሳሳይ ቃሎች ተጨምረውበታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤርምያስም ሌላ ክርታስ ወሰደ፤ ለኔርዩም ልጅ ለጸሓፊው ለባሮክ ሰጠው፤ እርሱም የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአቄም በእሳት ያቃጠለውን የመጽሐፉን ቃል ሁሉ ከኤርምያስ አፍ ጻፈበት፤ ደግሞም እንደ ቀድሞው ያለ ቃል ብዙ ቃል ተጨመረበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤርምያስም ሌላ ክርታስ ወሰደ ለኔርያም ልጅ ለጸሐፊው ለባሮክ ሰጠው፥ እርሱም የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአቄም በእሳት ያቃጠለውን የመጽሐፉን ቃል ሁሉ ከኤርምያስ አፍ ጻፈበት፥ ደግሞም እንደ ቀድሞው ያለ ቃል ብዙ ቃል ተጨመረበት። |
ጌታ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ሁለት የድንጋይ ጽላቶች እንደ ፊተኞቹ አድርገህ ጥረብ፥ በሰበርኻቸው በፊተኞቹ ጽላቶች የነበሩትን ቃሎች እጽፍባቸዋለሁ።
ይሁዲም ሦስት ወይም አራት ዓምድ ያኽል ባነበበ ቍጥር፥ ንጉሡ ጸሐፊ በሚጠቀምበት ሰንጢ የተነበበለትን እየቀደደ ክርታሱ በሙሉ ፈጽሞ እስኪቃጠል ድረስ በምድጃ ውስጥ ወዳለው እሳት ይጥለው ነበር።
በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን የትንቢት ቃል ለሚሰማ ሁሉ እኔ እመሰክራለሁ፤ ማንም በዚህ ላይ አንዳች ቢጨምር፥ እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን መቅሠፍቶች ይጨምርበታል፤