ወደ ንጉሡ ቤት ወደ ጸሐፊው ጓዳ ወረደ፤ እነሆም፥ አለቆች ሁሉ፥ ጸሐፊው ኤሊሳማ፥ የሸማያ ልጅ ድላያ፥ የዓክቦር ልጅ ኤልናታን፥ የሳፋን ልጅ ገማርያ፥ የሐናንያ ልጅ ሴዴቅያስ አለቆቹም ሁሉ በዚያ ተቀምጠው ነበር።
ኤርምያስ 36:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክርታሱንም በጸሐፊው በኤሊሳማ ጓዳ አስቀምጠው ወደ ንጉሡ አደባባይ ገቡ፤ ቃሎቹንም ሁሉ በንጉሡ ጆሮ ተናገሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የብራናውን ጥቅልል በጸሓፊው በኤሊሳማ ክፍል ካስቀመጡት በኋላ፣ ንጉሡ ወዳለበት አደባባይ ሄደው የሆነውን ሁሉ ነገሩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባለ ሥልጣኖቹም የብራናውን ጥቅል በጸሐፊው በኤሊሻማዕ ክፍል አኖሩት፤ ወደ ንጉሥም አደባባይ ሄደው የሆነውን ነገር ሁሉ አሳወቁት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ንጉሡም ወደ አደባባይ ገቡ፥ ክርታሱንም በጸሓፊው በኤሊሳማ ክፍል አኑረውት ነበር፤ ቃሉንም ሁሉ ለንጉሡ ተናገሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ንጉሡም ወደ አደባባይ ገቡ፥ ክርታሱንም በጸሐፊው በኤሊሳማ ጓዳ አኑረውት ነበር፥ ቃሉንም ሁሉ በንጉሡ ጆሮ ተናገሩ። |
ወደ ንጉሡ ቤት ወደ ጸሐፊው ጓዳ ወረደ፤ እነሆም፥ አለቆች ሁሉ፥ ጸሐፊው ኤሊሳማ፥ የሸማያ ልጅ ድላያ፥ የዓክቦር ልጅ ኤልናታን፥ የሳፋን ልጅ ገማርያ፥ የሐናንያ ልጅ ሴዴቅያስ አለቆቹም ሁሉ በዚያ ተቀምጠው ነበር።
ንጉሡም ክርታሱን እንዲያመጣ ይሁዲን ላከ፥ እርሱም ከጸሐፊው ከኤሊሳማ ጓዳ አመጣው፤ ይሁዲም በንጉሡና በንጉሡ አጠገብ በቆሙት አለቆች ሁሉ ጆሮ አነበበው።