ኤርምያስ 36:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም፦ “እስኪ ተቀመጥ፥ እየሰማንህም አንብብ” አሉት። ባሮክም እየሰሙት አነበበው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም፣ “እስኪ ተቀምጠህ አንብብልን” አሉት። ባሮክም አነበበላቸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም “በል ተቀመጥና ጽሑፉን አንብብልን!” አሉት፤ ባሮክም እንደታዘዘው አደረገ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም፥ “እስኪ ተቀመጥ፤ በጆሮአችንም አንብብ” አሉት። ባሮክም በጆሮአቸው አነበበው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም፦ እስኪ ተቀመጥ፥ በጆሮአችንም አንብብ አሉት። ባሮክም በጆሮአቸው አነበበው። |
ንጉሡም ክርታሱን እንዲያመጣ ይሁዲን ላከ፥ እርሱም ከጸሐፊው ከኤሊሳማ ጓዳ አመጣው፤ ይሁዲም በንጉሡና በንጉሡ አጠገብ በቆሙት አለቆች ሁሉ ጆሮ አነበበው።