ኤርምያስ 35:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የከባስን ልጅ የኤርምያስን ልጅ ያእዛንያን፥ ወንድሞቹንም፥ ልጆቹንም ሁሉ፥ የሬካባውያንን ወገን ሁሉ ወሰድኩ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ የካባስን ልጅ የኤርምያስን ልጅ ያእዛንያን፣ ወንድሞቹንና ወንዶች ልጆቹን ሁሉ፣ የሬካባውያንን ወገን በአጠቃላይ ሄጄ ጠራኋቸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እኔ የኤርምያስን ልጅ የአዛንያን፥ የሐባዲንያን ልጅ፥ ወንድሞቹንና ልጆቹን ሁሉ የሬካባውያንን ቤተሰብ በሙሉ ወሰድኩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የከባስንን ልጅ የኤርምያስን ልጅ ያእዛንያንና ወንድሞቹንም፥ ልጆቹንም ሁሉ የሬካባውያንን ቤተ ሰብእ ሁሉ ወሰድኋቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የከባስንን ልጅ የኤርምያስን ልጅ ያእዛንያን ወንድሞቹንም ልጆቹንም ሁሉ የሬካባውያንን ወገን ሁሉ ወሰድኋቸው፥ |
ወደ ጌታም ቤት የደጁ ጠባቂ በሆነው በሰሎም ልጅ በመዕሤያ ጓዳ በላይ ባለው በአለቆች ጓዳ አጠገብ ወደሚገኘው፥ ወደ እግዚአብሔር ሰው ወደ ጌዴልያ ልጅ ወደ ሐናን ልጆች ጓዳ አስገባኋቸው።