እነሆ፥ የሰሜንን ወገኖች ሁሉ እልካለሁ ይላል ጌታ፥ ባርያዬንም የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እወስዳለሁ፥ በዚህችም ምድር በሚቀመጡባትም ሰዎች፥ በዙሪያዋም ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ፤ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፥ ለመሣቀቂያና ለማፍዋጫም ለዘለዓለምም ባድማ አደርጋቸዋለሁ።
ኤርምያስ 35:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደዚህች ምድር በመጣ ጊዜ፦ ‘የከለዳውያንን ሠራዊትና የሶርያውያንን ሠራዊት በመፍራት ኑ ወደ ኢየሩሳሌም እንሂድ’ አልን፤ እንዲሁም በኢየሩሳሌም ተቀመጥን።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ይህችን ምድር በወረረ ጊዜ፣ ‘ኑ፤ ከባቢሎን ሰራዊትና ከሶርያ ሰራዊት ሸሽተን ወደ ኢየሩሳሌም እንሂድ’ ተባባልን፤ ስለዚህም በኢየሩሳሌም ተቀመጥን።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር መጥቶ አገሪቱን በወረረ ጊዜ ከባቢሎናውያንና ከሶርያውያን ሠራዊት ሸሽተን እናመልጥ ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም ለመምጣት ወስነናል፤ አሁንም በኢየሩሳሌም የምንኖረው ስለዚህ ነው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በዚች ምድር ላይ በዘመተ ጊዜ፦ ኑ ከከለዳውያን ሠራዊትና ከሶርያ ሠራዊት ፊት የተነሣ ወደ ኢየሩሳሌም እንሂድ፤ አልን፤ እንዲሁም በኢየሩሳሌም ተቀመጥን።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደዚህች ምድር በመጣ ጊዜ፦ ኑ ከከለዳውያን ሠራዊትና ከሶርያ ሠራዊት ፊት የተነሣ ወደ ኢየሩሳሌም እንሂድ አልን፥ እንዲሁም በኢየሩሳሌም ተቀመጥን። |
እነሆ፥ የሰሜንን ወገኖች ሁሉ እልካለሁ ይላል ጌታ፥ ባርያዬንም የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እወስዳለሁ፥ በዚህችም ምድር በሚቀመጡባትም ሰዎች፥ በዙሪያዋም ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ፤ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፥ ለመሣቀቂያና ለማፍዋጫም ለዘለዓለምም ባድማ አደርጋቸዋለሁ።
ዝም ብለን ለምን እንቀመጣለን? ጌታን ስለ በደልን አምላካችን ጌታ አጥፍቶናልና፥ የሐሞትንም ውኃ አጠጥቶናልና ተሰብሰቡ ወደ ተመሸጉ ከተሞች እንግባ በዚያም እንጥፋ።