La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 32:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በዓናቶትም ያለውን እርሻ ከአጐቴ ልጅ ከአናምኤል ገዛሁ፥ ዐሥራ ሰባት ሰቅል ብርም መዘንሁለት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ በዓናቶት ያለውን መሬት ከአጎቴ ልጅ ከአናምኤል ገዛሁ፤ ዐሥራ ሰባት ሰቅል ብር መዝኜ ሰጠሁት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

መሬቱንም ከሐናምኤል ለመግዛት ገንዘቡን መዘንኩለት፤ የዋጋውም ልክ ወደ ሁለት ኪሎ የሚመዝን ብር ሆነ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዐ​ና​ቶ​ትም ያለ​ውን እርሻ ከአ​ጎቴ ልጅ ከአ​ና​ም​ኤል ገዛሁ፤ ዐሥራ ሰባት ሰቅል ብርም መዘ​ን​ሁ​ለት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በዓናቶትም ያለውን እርሻ ከአጐቴ ልጅ ከአናምኤል ገዛሁ፥ አሥራ ሰባት ሰቅል ብርም መዘንሁለት።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 32:9
11 Referencias Cruzadas  

ግመሎቹም ከጠጡ በኋላ እንዲህ ሆነ፥ ሰውዬው ግማሽ ሰቅል የሚመዝን የወርቅ ቀለበት፥ ለእጆችዋም ዐሥር ሰቅል የሚመዘን ጥንድ የወርቅ አምባር አወጣ፥


የምድያም ነጋዶችም አለፉ፥ እነርሱም ዮሴፍን አንሥተው ከጉድጓድ አወጡት፥ ለእስማኤላውያንም ዮሴፍን በሃያ ብር ሸጡት፥ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብጽ ወሰዱት።


ንጉሡም በአጠገቡ ሲያልፍ፥ ነቢዩ ጠርቶ እንዲህ አለው፤ “ንጉሥ ሆይ! እኔ በጦርነት ውስጥ በውጊያ ላይ ነበርኩ፤ በዚያን ጊዜም ከወታደሮቹ አንዱ ከጠላት ወገን አንድን ሰው ማርኮ በማምጣት ‘ይህን ሰው ጠብቅ፤ ቢያመልጥ ግን በእርሱ ፈንታ አንተ ትገደላለህ ወይም ሠላሳ አራት ኪሎ የሚመዝን ጥሬ ብር መቀጫ ትከፍላለህ’ አለኝ።


ከእኔ በፊት የነበሩት የቀድሞ ገዢዎች ግን በሕዝቡ ላይ አክብደውባቸው ነበር፥ ምግብ፥ ወይና አርባ ሰቅል ብር ከእነሱ ይወስዱ ነበር፤ አገልጋዮቻቸው ደግሞ ሕዝቡን ይጨቁኑአቸው ነበር፤ እኔ ግን እግዚአብሔርን ስለ ፈራሁ እንዲህ አላደረግሁም።


በሬው ወንድ ባርያ ወይም ሴት ባርያ ቢወጋ፥ የበሬው ባለቤት ሠላሳ የብር ሰቅል ለጌታው ይስጥ፥ በሬው ግን ይወገር።


እንጀራ ላልሆነ ነገር ገንዘብን ለምን ታባክናላችሁ፥ የድካማችሁንም ዋጋ በማያጠግብ ነገር ለምን ትለውጣላችሁ? አድምጡኝ፥ በረከትንም ብሉ፥ ሰውነታችሁም በጮማ ደስ ይበለው።


የምትመገበውም ምግብ በሚዛን በየቀኑ ሃያ ሰቅል ይሁን፥ በየጊዜውም ትበላለህ።


እኔም በዓሥራ አምስት ብርና በአንድ ቆሮስ መስፈሪያ ተኩል ገብስ ገዛኋት።