ኤርምያስ 31:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በኤፍሬምም ተራሮች ላይ ያሉ ጠባቂዎች፦ ‘ተነሡ፥ ወደ ጽዮን ወደ አምላካችን ወደ ጌታ እንውጣ’ ብለው የሚጣሩበት ቀን ይመጣልና።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠባቂዎች፣ በኤፍሬም ኰረብቶች ላይ፣ ‘ኑ፤ ወደ ጽዮን፣ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር እንውጣ!’ ብለው የሚጮኹበት ቀን ይመጣል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠባቂዎች በኤፍሬም ተራራ ላይ ሆነው ‘ኑ አምላካችን እግዚአብሔር ወዳለበት ወደ ጽዮን እንሂድ’ የሚሉበት ጊዜ ይመጣል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኤፍሬም ተራሮች ላይ የሚከራከሩ፦ ተነሡ፤ ወደ ጽዮን ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር እንውጣ ብለው የሚጠሩባት ቀን ትመጣለችና።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኤፍሬምም ተራሮች ላይ ያሉ ጠባቆች፦ ተነሡ፥ ወደ ጽዮን ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር እንውጣ ብለው የሚጮኹበት ቀን ይመጣልና። |
እግዚአብሔር መንፈሳቸውን ያነሣሣው የይሁዳና የብንያም የአባቶች አለቆች፥ ካህናቱና ሌዋውያኑም ሁሉ ለመሄድና በኢየሩሳሌም ያለውን የጌታን ቤት ለመሥራት ተዘጋጁ።
በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ታላቅ መለከት ይነፋል፥ በአሦርም የጠፉ፥ በግብጽ ምድርም የተሰደዱ ይመጣሉ፤ በተቀደሰውም ተራራ በኢየሩሳሌም ለጌታ ይሰግዳሉ።
የምሥራች የምትነግሪ ጽዮን ሆይ፥ ከፍ ወደለው ተራራ ውጪ፤ የምሥራች የምትነግሪ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ድምፅሽን በኃይል አንሺ፤ አንሺ፥ አትፍሪ፤ ለይሁዳም ከተሞች፦ እነሆ፥ አምላካችሁ! ብለሽ ንገሪ።
ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ዘብ ጠባቂዎችን በቅጥሮችሽ ላይ አቁሜአለሁ፤ ቀንም ሆነ ሌሊት ከቶ ዝም አይሉም። እናንት ወደ ጌታ አቤት፤ አቤት የምትሉ፤ ፈጽሞ አትረፉ፤
ከዳተኞች ልጆች ሆይ! እኔ ጌታችሁ ነኝና ተመለሱ ይላል ጌታ፤ አንዱንም ከአንዲት ከተማ ሁለቱንም ከአንድ ወገን እወስዳችኋለሁ፥ ወደ ጽዮንም አመጣችኋለሁ፤”
ይመጣሉ በጽዮንም ተራራ ላይ ሆነው እልል ይላሉ፤ ስለ ጌታም በጎነቱ፥ ስለ እህሉና ስለ ወይን ጠጁ፥ ስለ ዘይቱም፥ ስለ በጎቹና ስለ ከብቶቹ በሐሤት ይሞላሉ፤ ነፍሳቸውም ውኃ ጠጥታ እንደ ረካች ገነት ትሆናለች፥ ከእንግዲህም ወዲህ አያዝኑም።
የሰው ልጅ ሆይ፥ ለሕዝብህ ልጆች ተናገር፥ እንዲህም በላቸው፦ ሰይፍን በምድር ላይ ባመጣሁ ጊዜ፥ የምድሪቱ ሕዝብ ከመካከላቸው አንድ ሰው ወስደው ለራሳቸው ዘበኛ ያደርጉታል፤