ሐናንያም በሕዝብ ሁሉ ፊት እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ “ጌታ እንዲህ ይላል፦ በሁለት ዓመት ውስጥ እንዲሁ የባቢሎንን ንጉሥ የናቡከደነፆርን ቀንበር ከአሕዛብ ሁሉ አንገት እሰብራለሁ።” ነቢዩም ኤርምያስ መንገዱን ሄደ።
ኤርምያስ 28:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ብሎ ተናግሮአል፦ የባቢሎንን ንጉሥ ቀንበር ሰብሬአለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘የባቢሎን ንጉሥ የጫነባችሁን ቀንበር እሰብራለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ብሎአል፥ ‘የባቢሎንን ንጉሥ ቀንበር እሰብራለሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የሠራዊት ጌታ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ የባቢሎንን ንጉሥ ቀንበር ሰብሬአለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ይናገራል፦ የባቢሎንን ንጉሥ ቀንበር ሰብሬአለሁ። |
ሐናንያም በሕዝብ ሁሉ ፊት እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ “ጌታ እንዲህ ይላል፦ በሁለት ዓመት ውስጥ እንዲሁ የባቢሎንን ንጉሥ የናቡከደነፆርን ቀንበር ከአሕዛብ ሁሉ አንገት እሰብራለሁ።” ነቢዩም ኤርምያስ መንገዱን ሄደ።
ባርያዎች እዳትሆኑአቸው ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ፤ የባርነታችሁን ቀንበር ሰብሬአለሁ፤ ቀና ብላችሁም እንድትሄዱ አድርጌአችኋለሁ።”
አለቆችዋ በጉቦ ይፈርዳሉ፥ ካህናቷ በክፍያ ያስተምራሉ፥ ነቢዮችዋ በብር ያሟርታሉ፤ “ጌታ በመካከላችን አይደለምን? ክፉ ነገር በእኛ ላይ አይመጣብንም” እያሉ በጌታ ይደገፋሉ።