La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 27:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም መንግሥት መጀመሪያ ይህ ቃል ከጌታ ዘንድ ወደ ኤርምያስ መጣ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በይሁዳ ንጉሥ፣ በኢዮስያስ ልጅ በሴዴቅያስ ዘመነ መንግሥት መጀመሪያ ላይ ይህ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የኢዮስያስ ልጅ ሴዴቅያስ በይሁዳ ከነገሠ በኋላ ወዲያውኑ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አ​ቄም መን​ግ​ሥት መጀ​መ​ሪያ ይህ ቃል ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ መጣ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም መንግሥት መጀመሪያ ይህ ቃል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ መጣ።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 27:1
8 Referencias Cruzadas  

ሴዴቅያስ በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሀያ አንድ ዓመት ነበር፤ መኖርያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ዐሥራ አንድ ዓመት ገዛ፤ እናቱም ሐሙጣል ተብላ የምትጠራ የልብና ከተማ ተወላጅ የነበረው የኤርምያስ ልጅ ነበረች፤


ሴዴቅያስ መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሀያ አንድ ዓመት ጎልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ።


በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም መንግሥት መጀመሪያ ይህ ቃል ከጌታ ዘንድ መጣ።


ለይሁዳ ንጉሥ ለሴዴቅያስም በእነዚህ ቃላት ሁሉ እንዲህ ብዬ ተናገርሁ፦ “ከባቢሎን ንጉሥ ቀንበር በታች አንገታችሁን ዝቅ አድርጉ ለእርሱና ለሕዝቡም አገልግሉአቸው በሕይወትም ኑሩ።


ወደ ይሁዳ ንጉሥም ወደ ሴዴቅያስ ወደ ኢየሩሳሌም በመጡት መልእክተኞች እጅ ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ፥ ወደ ሞዓብም ንጉሥ፥ ወደ አሞንም ልጆች ንጉሥ፥ ወደ ጢሮስም ንጉሥ፥ ወደ ሲዶናም ንጉሥ ትልካቸዋለህ።


በዚያም ዓመት፥ በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ መንግሥት መጀመሪያ፥ በአራተኛው ዓመት በአምስተኛው ወር፥ ነቢዩ የገባዖን ሰው የዓዙር ልጅ ሐናንያ በጌታ ቤት በካህናትና በሕዝብ ሁሉ ፊት እንዲህ ብሎ ተናገረኝ፦


በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ በአሥረኛው ዓመት፥ በናቡከደነፆር በዓሥራ ስምንተኛው ዓመት፥ ከጌታ ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው።