አንተ ግን፥ አቤቱ! እኔን ለመግደል በላዬ የመከሩትን ምክር ሁሉ ታውቃለህ፤ በደላቸውን ይቅር አትበል፥ ኃጢአታቸውንም ከፊትህ አትደምስስ፤ በፊትህም ይውደቁ፥ በቁጣህ ጊዜ እንዲሁ አድርግባቸው።
ኤርምያስ 26:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህናቱና ነቢያቱም ለአለቆቹና ለሕዝቡ ሁሉ፦ “በጆሮአችሁ እንደ ሰማችሁት በዚህች ከተማ ላይ ትንቢት ተናግሯልና ይህ ሰው ሞት ይገባዋል” ብለው ተናገሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህናቱና ነቢያቱም ለባለሥልጣኖቹና ለሕዝቡ ሁሉ፣ “በጆሯችሁ እንደ ሰማችሁት ይህ ሰው በዚህች ከተማ ላይ ትንቢት ስለ ተናገረ ሞት ይገባዋል” አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህናቱና ነቢያቱ ለመሪዎቹና ለሕዝቡ እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሰው የተናገረውን ሁሉ እናንተ ራሳችሁ ሰምታችሁታል፤ በከተማችን ላይ ክፉ የትንቢት ቃል በመናገሩ ሞት ይገባዋል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህናቱና ነቢያተ ሐሰትም ለአለቆቹና ለሕዝቡ ሁሉ፥ “በጆሮአችሁ እንደ ሰማችሁ በዚች ከተማ ላይ ትንቢት ተናግሮአልና ይህ ሰው ሞት የሚገባው ነው” ብለው ተናገሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህናቱና ነቢያቱም ለአለቆቹና ለሕዝቡ ሁሉ፦ በጆሮአችሁ እንደ ሰማችሁ በዚህች ከተማ ላይ ትንቢት ተናግአልና ይህ ሰው ሞት የሚገባው ነው ብለው ተናገሩ። |
አንተ ግን፥ አቤቱ! እኔን ለመግደል በላዬ የመከሩትን ምክር ሁሉ ታውቃለህ፤ በደላቸውን ይቅር አትበል፥ ኃጢአታቸውንም ከፊትህ አትደምስስ፤ በፊትህም ይውደቁ፥ በቁጣህ ጊዜ እንዲሁ አድርግባቸው።
አለቆቹም ንጉሡን፦ “ይህን የመሰለውን ቃላት እየነገራቸው የሕዝቡን ሁሉ እጅ በዚህችም ከተማ የቀሩትን የወታደሮቹን እጅ እያደከመ ነውና ይህ ሰው እንዲገደል እንለምንሃለን፤ ይህ ሰው ክፋትን እንጂ ለዚህ ሕዝብ ሰላምን አይመኝለትምና” አሉት።
እስከዚህም ቃል ድረስ ይሰሙት ነበር፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው፥ “እነደዚህ ያለውን ሰው ከምድር አስወግደው፤ በሕይወት ይኖር ዘንድ አይገባውምና፤” አሉ።
የከተማይቱም ሰዎች ኢዮአስን፥ “የበኣልን መሠዊያ ያፈረሰና በአጠገቡ የቆመውን የአሼራን ምስል ዐምድ የሰበረው ልጅህ በመሆኑ መሞት ስላለበት አውጣልን አሉት።”