ኤርምያስ 25:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ማሰማርያቸውን አጥፍቶአልና የእረኞች ጩኸት ድምፅ የመንጋ አውራዎችም ልቅሶ ሆኖአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ማሰማሪያቸውን አጥፍቷልና፣ የእረኞችን ጩኸት፣ የመንጋ ጠባቂዎችን ዋይታ ስሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እረኞቹ ይጮኻሉ፤ እግዚአብሔር የመንጋዎቻቸውን መሰማሪያ ስላጠፋ የመንጋዎቹ ባለቤቶች ምርር ብለው ያለቅሳሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ማሰማርያቸውን አጥፍቶአልና የእረኞች ጩኸት ድምፅ፥ የበጎች አውራዎችም ልቅሶ ሆኖአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ማሰማርያቸውን አጥፍቶአልና የእረኞች ጩኸት ድምፅ የመንጋ አውራዎችም ልቅሶ ሆኖአል። |
“ልትታረዱና ልትበተኑ ቀናችሁ ደርሶአልና፥ እንደ ተወደደም የሸክላ ዕቃ ትወድቃላችሁና እናንተ እረኞች፥ አልቅሱ ጩኹም፤ እናንተ የመንጋ አውራዎች፥ በአመድ ውስጥ ተንከባለሉ።