La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 2:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“ስለዚህ ከእናንተ ጋር ገና እከራከራለሁ፥ ይላል ጌታ፥ ከልጆቻችሁም ልጆች ጋር እከራከራለሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ስለዚህ እንደ ገና ከእናንተ ጋራ እፋረዳለሁ፤ ከልጅ ልጆቻችሁም ጋራ እከራከራለሁ።” ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“ስለዚህ እኔ እግዚአብሔር ገና እናንተን ሕዝቤን እወቅሳለሁ፤ በልጆቻችሁም ላይ ወቀሳ አቀርባለሁ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“ስለ​ዚህ እንደ ገና ከእ​ና​ንተ ጋር እከ​ራ​ከ​ራ​ለሁ፤ ከል​ጆ​ቻ​ች​ሁም ልጆች ጋር እከ​ራ​ከ​ራ​ለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ስለዚህ ከእናንተ ጋር እከራከራለሁ፥ ከልጆቻችሁም ልጆች ጋር እከራከራለሁ።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 2:9
12 Referencias Cruzadas  

በላይ ያለውን ሰማይን ምድርንም እንዲሁ በሕዝቡ ለመፍረድ ይጠራል፥


አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውም፤ እኔ ጌታ አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፥


ጌታ በፍርድ ወንበር ላይ ተቀምጦአል፤ በሕዝቡም ላይ ለመፍረድ ተነሥቶአል።


አሳስበኝ፥ በአንድነትም ሆነን እንፋረድ፤ እንድትጸድቅ ነገርህን ተናገር።


“ከእኔ ጋር የምትከራከሩት ለምንድን ነው? ሁላችሁ ዐምፃችሁብኛል ይላል ጌታ።


አንቺ ግን፦ ‘እኔ ንጹሕ ነኝ፤ በእውነት ቁጣው ከእኔ ተመልሶአል’ አልሽ። እነሆ፦ ‘ኃጢአት አልሠራሁም’ ብለሻልና በፍርድ እከስሻለሁ።


ጌታም ደግሞ ከይሁዳ ጋር ሙግት አለው፥ ያዕቆብንም እንደ መንገዱ ይቀጣል፤ እንደ ሥራውም ይመልስለታል።


የይሁዳ ልጆችና የእስራኤል ልጆች በአንድነት ይሰበሰባሉ፥ እነርሱም አንድ አለቃ በራሳቸው ላይ ይሾማሉ፤ የኢይዝራኤልም ቀን ታላቅ ይሆናልና ከምድሪቱ ይወጣሉ።


እናንተ የእስራኤል ልጆች ሆይ! እውነትና ጽኑ ፍቅር አምላክንም ማወቅ በምድሪቱ ስለ ሌለ ጌታ በምድሪቱ ላይ ከሚኖሩ ጋር ሙግት አለውና የጌታን ቃል ስሙ።


እኔ በዚያ ሰውና በቤተሰቡ ላይ ፊቴን አጠቊርበታለሁ፤ እርሱንም፥ ከሞሌክም ጋር ለማመንዘር የሚከተሉትን ሁሉ ከሕዝባቸው መካከል ለይቼ አጠፋለሁ።


ተራሮች ሆይ፥ ጠንካሮች የምድር መሠረቶችም ሆይ፥ የጌታን ወቀሳ ስሙ፤ ጌታ ከሕዝቡ ጋር ክርክር አለውና፥ ከእስራኤልም ጋር ይዋቀሳልና።