ኤርምያስ 17:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እንዲህ ይለኛል፦ “ሂድ፥ የይሁዳም ነገሥታት በሚገቡበትና በሚወጡበት በሕዝቡ ልጆች በር፥ በኢየሩሳሌምም በሮች ሁሉ ቁም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “ሄደህ የይሁዳ ነገሥታት በሚገቡበትና በሚወጡበት በሕዝቡ በር በሌሎቹም የኢየሩሳሌም በሮች ሁሉ ቁም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “የይሁዳ ንጉሥ ከከተማይቱ በሚወጣበትና በሚገባበት ወደ ሕዝቡ ቅጽር በር እንዲሁም በኢየሩሳሌም ወደሚገኙት ወደ ሌሎቹም ቅጽር በሮች ሄደህ ቁም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛል፥ “ሂድ፤ የይሁዳም ነገሥታት በሚገቡበትና በሚወጡበት በሕዝብህ ልጆች በር በኢየሩሳሌምም በሮች ሁሉ ቁም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛል፦ ሂድ፥ የይሁዳም ነገሥታት በሚገቡበትና በሚወጡበት በሕዝቡ ልጆች በር በኢየሩሳሌምም በሮች ሁሉ ቁም፥ |
“ጌታ እንዲህ ይላል፦ በጌታ ቤት አደባባይ ቁም፥ በጌታም ቤት ውስጥ ለመስገድ ለሚመጡት ለይሁዳ ከተሞች ሁሉ እንድትናገራቸው ያዘዝሁህን ቃላት ሁሉ ተናገር፤ አንዲትም ቃል አትጉድል።
ባሮክም የኤርምያስን ቃላት በላይኛው አደባባይ በጌታ ቤት በአዲሱ በር መግቢያ ባለው በጸሐፊው በሳፋን ልጅ፥ በገማርያ ጓዳ በጌታ ቤት ውስጥ በሕዝቡ ሁሉ ጆሮ ከመጽሐፉ አነበበ።
አንተ ግን ሂድ፥ እየነገርሁህም የጻፍኸውን የጌታን ቃላት በጾም ቀን በጌታ ቤት በሕዝቡ ጆሮ ከክርታሱ አንብብ፤ እንዲሁም ደግሞ ከከተሞቻቸው በሚወጡ በይሁዳ ሰዎች ሁሉ ጆሮ አንብበው።
“በጌታ ቤት በር ቁም፥ ይህንም ቃል በዚያ እንዲህ ብለህ አውጅ፦ ጌታን ልታመልኩ በእነዚህ በሮች የምትገቡ የይሁዳ ሰዎች ሆይ! ሁላችሁ የጌታን ቃል ስሙ።