La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢሳይያስ 8:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከእነርሱ ብዙዎች ይሰናከላሉ፤ ይወድቃሉ፤ ይሰበራሉ፤ ወጥመድ ይገባሉ፤ ይያዛሉም።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከእነርሱ ብዙዎች ይሰናከላሉ፤ ይወድቃሉ፤ ይሰበራሉ፤ ወጥመድ ይገባሉ፤ ይያዛሉም።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ ብዙዎች ይሰናከላሉ፤ ወድቀውም ይሰባበራሉ፤ በወጥመድ ተይዘውም ይወሰዳሉ።”

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ስለ​ዚ​ህም ከእ​ነ​ርሱ ብዙ​ዎች በእ​ርሱ ይሰ​ና​ከ​ላሉ፤ ይወ​ድ​ቁ​ማል፤ ይሰ​በ​ሩ​ማል፤ ይጠ​መ​ዱ​ማል፤ ይያ​ዙ​ማል።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ብዙዎችም በእርሱ ይሰናከላሉ፥ ይወድቁማል፥ ይሰበሩማል፥ ይጠመዱማል፥ ይያዙማል።

Ver Capítulo



ኢሳይያስ 8:15
12 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ ሄደው ወደ ኋላ እንዲወድቁ፥ እንዲሰበሩም፥ በወጥመድም እንዲያዙ፥ የጌታ ቃል በትእዛዝ ላይ ትእዛዝ፥ በትእዛዝ ላይ ትእዛዝ፥ በደንብ ላይ ደንብ፥ በደንብ ላይ ደንብ፤ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ ይሆንላቸዋል።


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በጽዮን ድንጋይን ለመሠረት አስቀምጣለሁ፤ የተፈተነውን፥ የከበረውን፥ መሠረቱ የጸናውን የማዕዘን ድንጋይ፤ “የሚያምን አያፍርም።”


እንደ ዕውሮች ወደ ቅጥሩ ተርመሰመስን፥ ዐይን እንደሌላቸው ተርመሰመስን፤ በቀትር ጊዜ በድግዝግዝታ እንዳለ ሰው ተሰናከልን፥ እንደ ሙታን በጨለማ ስፍራ ነን።


ከሚሰጡትም የተትረፈረፈ ወተት ቅቤ ይበላል፤ በምድሪቱም የቀሩ ሁሉ ቅቤና ማር ይበላሉ።


ስለዚህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፥ ከዚህ ሕዝብ ፊት ዕንቅፋቶችን አደርጋለሁ፤ አባቶችና ልጆች በአንድነት ይሰናከሉባቸዋል፥ ጎረቤትና ባልንጀራውም ይጠፋሉ።’ ”


በእኔ የማይሰናከል ሁሉ የተባረከ ነው።”


ተዉአቸው፤ ዕውሮችን የሚመሩ ዕውሮች ናቸው፤ ዕውር ዕውርን ቢመራ ሁለቱም ወደ ጉድጓድ ይወድቃሉ።”


በዚህ ድንጋይ ላይ የሚወድቅ ይሰባበራል፤ ድንጋዩ በላዩ ላይ የሚወድቅበትን ሁሉ ግን ያደቅቀዋል።”


በዚህም ምክንያት ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎች ወደ ኋላ ተመለሱ፤ ወደፊትም ከእርሱ ጋር ወደ ፊት መሄድም አቆሙ።


ለምን? ምክንያቱም በእምነት ሳይሆን በሥራ እንደሆነ ስለቆጠሩት ነው፤ ስለዚህ በማሰናከያ ድንጋይ ተሰናከሉ።


እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው፤