ኢሳይያስ 7:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ቀን ሺህ ሰቅል ብር የሚያወጣ አንድ ሺህ የወይን ተክል የነበረበት ቦታ ሁሉ፤ ኩርንችትና እሾኽ ብቻ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ቀን ሺሕ ሰቅል ብር የሚያወጣ አንድ ሺሕ የወይን ተክል የነበረበት ቦታ ሁሉ፣ ኵርንችትና እሾኽ ብቻ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በዚያም ቀን ግምቱ ሺህ ብር የሚሆን አንድ ሺህ ምርጥ የወይን ተክል እንዲለማ የተደረገበት ቦታ ሁሉ ኲርንችትና እሾኽ ይበቅልበታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ወራት እንዲህ ይሆናል፤ ወይን በሀገሩ ሁሉ የበጀ ይሆናል፤ የአንድ ሺህ የወይን ዳስ ዋጋ አንድ ሺህ የብር ሰቅል ይሆናል። ከዚህ በኋላ ዳግመኛ ምድር ሁሉ ትጠፋለች፤ እሾህንና ኵርንችትንም ትሞላለች፤ ፍርሀትም ይመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፥ ሺህ ብር የተገመተ ሺህ የወይን ግንድ በነበረበት ሥፍራ ሁሉ ለኵርንችትና ለእሾህ ይሆናል። |
እናንተ ተማምናችሁ የምትቀመጡ ሴቶች ሆይ፥ ወይንን መቁረጥ ይጠፋልና፥ ፍሬም ማከማቸት አይመጣምና ከዓመትና ከጥቂት ቀን በኋላ ትንቀጠቀጣላችሁ።
ከሩብ ጋሻ የወይን ቦታ አንድ የባዶስ መስፈሪያ ያህል የወይን ጭማቂ ብቻ ይገኛል፤ አንድ የቆሮስ መስፈሪያ ዘር ተዘርቶ አንድ የኢፍ መስፈሪያ እህል ብቻ ይሰጣል።
እነሆ፥ ከጥፋት ሸሽተው ቢሄዱ እንኳ ግብጽ ትሰበስባቸዋለች፥ ሜምፎስም ትቀብራቸዋለች፤ ሳማም የብራቸውን ጌጥ ይወርሰዋል፥ እሾኽም በድንኳኖቻቸው ውስጥ ይበቅላል።
“ሌላም ምሳሌ ስሙ፤ የወይን አትክልት የተከለ አንድ የእርሻ ባለቤት ነበረ፤ እርሱም ቅጥር ቀጠረለት፤ መጭመቂያም ማሰለት፤ ግንብም ሠራለት፤ እርሻውንም ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ።