እነርሱም፦ “ሕዝቅያስ እንዲህ ይላል፦ ይህ ቀን የመከራና የተግሣጽ የዘለፋም ቀን ነው፤ ልጆች የሚወለዱበት ጊዜ ደርሶአል ለመውለድም ብርታቱ የለም።
ኢሳይያስ 66:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳታምጥ ወለደች፤ ምጥም ሳያስጭንቃት ወንድ ልጅን ወለደች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከማማጧ በፊት፣ ትወልዳለች፤ በምጥ ጣር ከመያዟ በፊት፣ ወንድ ልጅ ትገላገላለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጽዮን ምጥ ሳይጀምራት እንደ ወለደች፥ የምጥ ስሜት ሳይሰማት እንደ ተገላገለች ሴት ነች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሳታምጥ ወለደች፤ ምጥም ሳያገኛት ወንድ ልጅን ወለደች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳታምጥ ወለደች፥ ምጥም ሳያገኛት ወንድ ልጅን ወለደች። |
እነርሱም፦ “ሕዝቅያስ እንዲህ ይላል፦ ይህ ቀን የመከራና የተግሣጽ የዘለፋም ቀን ነው፤ ልጆች የሚወለዱበት ጊዜ ደርሶአል ለመውለድም ብርታቱ የለም።
አንቺ ያልወለድሽ መካን ሆይ፥ ዘምሪ፤ አንቺ ያላማጥሽ ሆይ፥ እልል በዪ፥ ጩኺም፤ ባል ካላት ይልቅ ፈት የሆነቺቱ ልጆች በዝተዋልና፥ ይላል ጌታ።
ሴት በምትወልድበት ጊዜ ወራትዋ ስለ ደረሰ ታዝናለች፤ ነገር ግን ሕፃን ከወለደች በኋላ፥ ሰው በዓለም ተወልዶአልና በደስታዋ ምክንያት መከራዋን ከቶውን አታስበውም።