ኢሳይያስ 65:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቤትም ይሠራሉ ይኖሩበታል፤ ወይንም ይተክላሉ ፍሬውንም ይበላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎች ቤት ይሠራሉ፤ በውስጡም ይኖራሉ፤ ወይንን ይተክላሉ፤ ፍሬውንም ይበላሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቤ ቤት ሠርተው ይኖሩበታል፤ ወይን ተክለው ፍሬውን ይበላሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቤቶችንም ይሠራሉ፤ ይቀመጡባቸውማል፤ ወይኑን ይተክላሉ፤ ፍሬውንም ይበላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቤቶችንም ይሠራሉ ይቀመጡባቸውማል፥ ወይኑንም ይተክላሉ ፍሬውንም ይበላሉ። |
በምድርም ለተዘራው ዘርህ ዝናብ ይሰጣል፥ ከምድርም ፍሬ የሚወጣ እንጀራ ወፍራምና ብዙ ይሆናል። በዚያም ቀን ከብቶችህ በሰፊ መስክ ይሰማራሉ፤
ይህ ምልክት ይሆንሃል፤ በዚህ ዓመት የገቦውን፥ በሁለተኛውም ዓመት ከገቦው የበቀለውን ትበላላችሁ፤ በሦስተኛውም ዓመት ትዘራላችሁ ታጭዳላችሁ፤ ወይንም ትተክላላችሁ፤ ፍሬውንም ትበላላችሁ።
እኔ ደግሞ እንዲህ አደርግባችኋለሁ፤ ፍርሃትን፥ ነፍስን የሚያኮስስና ዓይንን የሚያፈዝዝ ክሳትና ትኩሳት አመጣባችኋለሁ፤ ጠላቶቻችሁም ይበሉታልና ዘራችሁን በከንቱ ትዘራላችሁ።
የሕዝቤን የእስራኤልን ምርኮ እመልሳለሁ፥ የፈረሱትንም ከተሞች ዳግም ሠርተው ይቀመጡባቸዋል፤ ወይንንም ይተክላሉ፥ የወይን ጠጁንም ይጠጣሉ፤ የአትክልት ስፍራዎችንም ያበጃሉ፥ ፍሬውንም ይበላሉ።