ኢሳይያስ 63:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተቀደሰው ሕዝብህ መቅደስህን ጥቂት ጊዜ ወረሱት፤ ጠላቶቻችንም መቅደስን ረግጠውታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለጥቂት ጊዜ ሕዝብህ የተቀደሰውን ስፍራ ወርሶ ነበር፤ አሁን ግን ጠላቶቻችን መቅደስህን ረገጡት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለጥቂት ጊዜ ቤተ መቅደስህ የቅዱስ ሕዝብህ ንብረት ነበር፤ አሁን ግን ጠላቶቻችን ረገጡት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተቀደሰው ተራራህ ከርስትህ ጥቂት ክፍል እናገኝ ዘንድ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተቀደሰው ሕዝብህ መቅደስህን ጥቂት ጊዜ ወረሱት፥ ጠላቶቻችንም ረግጠውታል። |
ከፈጠራቸውም አሕዛብ ሁሉ በምስጋናና በስም፥ በክብር ከፍ እንደሚያደርግህና እርሱም እንደ ተናገረ ለጌታ እግዚአብሔር ቅዱስ ሕዝብ አደረገህ።”
እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን አስደናቂ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ እግዚአብሔር ለራሱ ያደረጋችሁ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ።
ከመቅደሱ ውጭ ያለውን አደባባይ ግን ተወው፤ አትለካውም፥ ምክንያቱም ለአሕዛብ ተሰጥቶአልና፤ እነርሱም ለአርባ ሁለት ወር ያህል የተቀደሰችውን ከተማ ይረግጡአታል።