Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 63:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 በተ​ቀ​ደ​ሰው ተራ​ራህ ከር​ስ​ትህ ጥቂት ክፍል እና​ገኝ ዘንድ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ለጥቂት ጊዜ ሕዝብህ የተቀደሰውን ስፍራ ወርሶ ነበር፤ አሁን ግን ጠላቶቻችን መቅደስህን ረገጡት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 የተቀደሰው ሕዝብህ መቅደስህን ጥቂት ጊዜ ወረሱት፤ ጠላቶቻችንም መቅደስን ረግጠውታል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ለጥቂት ጊዜ ቤተ መቅደስህ የቅዱስ ሕዝብህ ንብረት ነበር፤ አሁን ግን ጠላቶቻችን ረገጡት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 የተቀደሰው ሕዝብህ መቅደስህን ጥቂት ጊዜ ወረሱት፥ ጠላቶቻችንም ረግጠውታል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 63:18
21 Referencias Cruzadas  

ዮሴ​ፍን እንደ መንጋ የም​ት​መራ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ጠባቂ ሆይ፥ አድ​ምጥ፤ በኪ​ሩ​ቤል ላይ የም​ት​ቀ​መጥ፥ ተገ​ለጥ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “የተ​ቤ​ዣ​ቸው፥ የተ​ቀ​ደሰ ሕዝብ” ብለው ይጠ​ሩ​አ​ቸ​ዋል፤ አን​ቺም፥ “የተ​ተ​ወች ያይ​ደ​ለች የተ​ወ​ደ​ደች ቅድ​ስት ከተማ” ትባ​ያ​ለሽ።


ከጥ​ንት እን​ዳ​ል​ገ​ዛ​ኸን ስም​ህም በእኛ ላይ እን​ዳ​ል​ተ​ጠራ ሆነ​ና​ልና።


የተ​ቀ​ደሱ ከተ​ሞ​ችህ ምድረ በዳ ሆነ​ዋል፤ ጽዮን ምድረ በዳ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ውድማ ሆና​ለች።


አቤቱ፥ እጅግ አት​ቈጣ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ኀጢ​አ​ታ​ች​ንን አታ​ስብ፤ አሁ​ንም እባ​ክህ፥ ወደ እኛ ተመ​ል​ከት፤ እኛ ሁላ​ችን ሕዝ​ብህ ነን።


ብዙ እረ​ኞች የወ​ይ​ኑን ቦታ​ዬን አጥ​ፍ​ተ​ዋል፤ እድል ፈን​ታ​ዬ​ንም አር​ክ​ሰ​ዋል፤ የም​ወ​ድ​ዳ​ት​ንም እድል ፈንታ ምድረ በዳ አድ​ር​ገ​ዋ​ታል።


ዮድ። አስ​ጨ​ና​ቂው በም​ኞቷ ሁሉ ላይ እጁን ዘረጋ፤ ወደ ጉባ​ኤህ እን​ዳ​ይ​ገቡ ያዘ​ዝ​ሃ​ቸው አሕ​ዛብ ወደ መቅ​ደ​ስዋ ሲገቡ አይ​ታ​ለ​ችና።


አሌፍ። ወርቁ እን​ዴት ደበሰ! ጥሩው ብር እን​ዴት ተለ​ወጠ! የከ​በ​ረው ዕንቍ በጎ​ዳ​ናው ሁሉ እን​ዴት ተበ​ተነ!


ከተ​ሞ​ቻ​ች​ሁ​ንም ባድማ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ መቅ​ደ​ሶ​ቻ​ች​ሁ​ንም አፈ​ር​ሳ​ለሁ፤ የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁ​ንም መዓዛ አላ​ሸ​ት​ትም።


መሳ​ቂያ የሆኑ የኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገ​ጃ​ዎች ይፈ​ር​ሳሉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም መቅ​ደ​ሶች ባድማ ይሆ​ናሉ፤ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ቤት ላይ በሰ​ይፍ እነ​ሣ​ለሁ” አለ።


እርሱ ግን መልሶ “ይህን ሁሉ ታያላችሁን? እውነት እላችኋለሁ፥ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም፤” አላቸው።


በሰ​ይፍ ስለት ይወ​ድ​ቃሉ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም ሁሉ ይማ​ረ​ካሉ፤ የአ​ሕ​ዛብ ጊዜ​ያ​ቸው እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ አሕ​ዛብ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ይረ​ግ​ጡ​አ​ታል።


ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ በላይ ትሆን ዘንድ፥ እር​ሱም እንደ ተና​ገረ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ሕዝብ ትሆን ዘንድ ታላቅ ስምን፥ ምስ​ጋ​ናና ክብ​ር​ንም አደ​ረ​ገ​ልህ።”


“ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንተ ቅዱስ ሕዝብ ነህና፤ በም​ድር ፊት ከሚ​ኖሩ አሕ​ዛብ ሁሉ ይልቅ ለእ​ርሱ ለራሱ ሕዝብ ትሆ​ን​ለት ዘንድ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መር​ጦ​ሃ​ልና።


እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤


በመቅደሱም ውጭ ያለው እድሞ ለአሕዛብ ተሰጥቶአልና ተወው፤ አትለካውም፤ እነርሱም አርባ ሁለት ወር የተቀደሰችውን ከተማ ይረግጡአታል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos