አሕዛብ ይገዙልህ ሕዝብም ይስገዱልህ፥ ለወንድሞችህ ጌታ ሁን፥ የእናትህም ልጆች ይስገዱልህ፥ የሚረግምህ እርሱ ርጉም ይሁን የሚባርክህም ቡሩክ ይሁን።”
ኢሳይያስ 60:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአንቺም የማይገዛ ሕዝብና መንግሥት ይጠፋል፥ እነዚያ አሕዛብም ፈጽመው ይጠፋሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለአንቺ የማይገዛ ሕዝብና መንግሥት ይጠፋል፤ ፈጽሞም ይደመሰሳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንቺን የማያገለግሉ ሕዝቦችና መንግሥቶች ግን ፈጽመው ይጠፋሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለአንቺም የማይገዙ ነገሥታት ይሞታሉ፤ እነዚያም አሕዛብ ፈጽመው ይጠፋሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአንቺም የማይገዛ ሕዝብና መንግሥት ይጠፋል፥ እነዚያ አሕዛብም ፈጽመው ይጠፋሉ። |
አሕዛብ ይገዙልህ ሕዝብም ይስገዱልህ፥ ለወንድሞችህ ጌታ ሁን፥ የእናትህም ልጆች ይስገዱልህ፥ የሚረግምህ እርሱ ርጉም ይሁን የሚባርክህም ቡሩክ ይሁን።”
አሕዛብም ይዘው ወደ ስፍራቸው ያመጡአቸዋል፥ የእስራኤልም ቤት በእግዚአብሔር ምድር እንደ ሎሌዎችና እንደ ገረዶች አድርገው ይገዙአቸዋል፤ የማረኩአቸውን ይማርካሉ፥ አስጨናቂዎችንም ይገዛሉ።
ሠረገላውንም ከኤፍሬም፥ ፈረሱንም ከኢየሩሳሌም አጠፋለሁ፤ የሰልፉም ቀስት ይሰበራል፥ ለአሕዛብም ሰላምን ይናገራል፤ ግዛቱም ከባሕር እስከ ባሕር፥ ከወንዙም እስከ ምድር ዳርቻ ድርስ ይሆናል።