ኢሳይያስ 54:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የግንብሽንም ጉልላት በቀይ ዕንቁ፥ በሮችሽንም በሚያብረቀርቅ ዕንቁ፥ ዳርቻሽንም ሁሉ በከበሩ ድንጋዮች እሠራለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጕልላትሽን በቀይ ዕንቍ፣ በሮችሽን በሚያብረቀርቁ ዕንቍዎች፣ ቅጥሮችሽንም በከበሩ ድንጋዮች እሠራለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የግንቦችሽን ጒልላት በቀይ መረግድ፥ የቅጽር በሮችሽንም በሚያብረቀርቅ ዕንቊ፥ በዙሪያሽ ያለውንም ቅጽር በከበሩ ድንጋዮች አንጻለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ግንብሽንም በቀይ ዕንቍ፥ በሮችሽንም ቢረሌ በተባለ ዕንቍ፥ ዳርቻዎችሽንም በከበረ ዕንቍ እሠራለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የግንብሽንም ጕልላት በቀይ ዕንቍ፥ በሮችሽንም በሚያብረቀርቅ ዕንቍ፥ ዳርቻሽንም ሁሉ በከበሩ ድንጋዮች እሠራለሁ። |
የከተማይቱ በሮች በእስራኤል ነገዶች ስም ይጠራሉ፤ በሰሜን በኩል ሦስት በሮች አሉ፥ አንዱ የሮቤል በር፥ አንዱ የይሁዳ በር፥ አንዱ ደግሞ የሌዊ በር ነው።
በዚያም ቀን አምላካቸው ጌታ ሕዝቡን እንደ መንጋ ያድናቸዋል፤ እነርሱም ለአክሊል እንደሚሆኑ እንደ ከበሩ ድንጋዮች ይሆናሉ፥ በምድሩም ላይ ያበራሉ።
ታላቅና ረጅም ቅጥር ነበራት፤ ዐሥራ ሁለትም ደጆች ነበሩአት፤ በደጆቹም ዐሥራ ሁለት መላእክት ቆመው ነበር፤ የዐሥራ ሁለቱም የእስራኤል ልጆች ነገዶች ስሞች ተጽፈውባቸው ነበር።