ኢሳይያስ 53:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ፤ ሕመማችንንም ተሸከመ፤ እኛ ግን እንደ ተመታ፥ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ፥ እንደ ስቃይተኛም ቈጠርነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በርግጥ እርሱ ደዌያችንን ወሰደ፤ ሕመማችንንም ተሸከመ፤ እኛ ግን በእግዚአብሔር እንደ ተመታ፣ እንደ ተቀሠፈ፣ እንደ ተሠቃየም ቈጠርነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በእውነት እርሱ ደዌአችንን ተቀበለ፤ ሕማማችንንም ተሸከመ፤ እኛ ግን በእግዚአብሔር ተመትቶ እንደ ወደቀና እንደ ቈሰለ አድርገን ቈጠርነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ ግን በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ፤ ሕመማችንንም ተሸከመ፤ ስለ እኛም ታመመ፤ እኛም እንደ ታመመ፥ እንደ ተገረፈም ቈጠርነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፥ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው። |
ጌታም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የጌታም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።
ለዐዛዜል ይሆን ዘንድ ዕጣው የወደቀበትን ፍየል እንዲያስተሰርይበት፥ ወደ ምድረ በዳ እንዲሄድ ለመልቀቅ በሕይወቱ እንዳለ በእግዚአብሔር ፊት ያቆመዋል።
ሰይፍ ሆይ፥ ባልንጀራዬ በሆነው ሰው በእረኛዬ ላይ ንቃ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ፤ በጎቹም እንዲበተኑ እረኛውን ምታ፤ እጄንም በታናናሾች ላይ አዞራለሁ።
እንዲሁም ክርስቶስ፥ የብዙዎችን ኃጢአት ሊሸከም አንድ ጊዜ ተሰውቷል። ለሁለተኛ ጊዜ ሲታይ ሊያድናቸው ለሚጠባበቁት ኃጢአትን ለመሸከም ሳይሆን መዳንን ለማምጣት ነው።
ክርስቶስ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዐመፀኞች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ስለ ኃጢአት መከራን ተቀበለ፤ እርሱ ወደ እግዚአብሔር ሊያቀርባችሁ በሥጋ ሞተ፥ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ።