Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘሌዋውያን 16:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ለዐዛዜል ይሆን ዘንድ ዕጣው የወደቀበትን ፍየል እንዲያስተሰርይበት፥ ወደ ምድረ በዳ እንዲሄድ ለመልቀቅ በሕይወቱ እንዳለ በእግዚአብሔር ፊት ያቆመዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ወደ ምድረ በዳ ተለቅቆ ማስተስረያ ይሆን ዘንድ፣ እንዲለቀቅ ዕጣ የወጣበትን ፍየል ከነሕይወቱ በእግዚአብሔር ፊት ያቅርብ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ለዐዛዜል የተመረጠውም ፍየል የሕዝቡን ኃጢአት ተሸክሞ ወደ በረሓ እንዲላክ ከነሕይወቱ ወደ እግዚአብሔር ፊት ይቀርባል።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 የመ​ለ​ቀ​ቅም ዕጣ የሆ​ነ​በ​ትን ፍየል ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​በት ዘንድ፥ ለመ​ለ​ቀ​ቅም ወደ ምድረ በዳ ይሰ​ድ​ደው ዘንድ በሕ​ይ​ወቱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቆ​መ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 የመለቀቅም ዕጣ የሆነበትን ፍየል ያስተሰርይበት ዘንድ፥ ለመለቀቅም ወደ ምድረ በዳ ይሰድደው ዘንድ በሕይወቱ በእግዚአብሔር ፊት ያቆመዋል።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 16:10
12 Referencias Cruzadas  

እርሱም የኃጢአታችን ማስተስረያ ነው፥ ለእኛ ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ለዓለሙ ሁሉ ኃጢአት እንጂ።


እርሱ ስለ እኛ ሕይወቱን አሳልፎ ስለ ሰጠን በዚህ ፍቅርን አውቀናል፤ እኛም ስለ ወንድሞቻችን ሕይወታችንን አሳልፈን ልንሰጥ ይገባናል።


እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንድንሆን ስለ እኛ ኃጢአት የሌለበትን እርሱን ኃጢአት አደረገው።


ስለ ኃጢአታችን ለሞት ተላልፎ ተሰጠ፤ ለጽድቃችንም ተነሣ።


እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ ያቀረበው ነው፤ ይህም በእግዚአብሔር ትዕግስት በፊት የተደረገውን ኃጢአት በመተው ጽድቁን እንዲያሳይ ነው፤


ከለምጽ ደዌ በሚነጻው ሰው ላይ ሰባት ጊዜ ይረጨዋል፤ ከዚያም ንጹሕ ነህ ይለዋል፥ በሕይወትም ያለውን ወፍ በተንጣለለው ሜዳ ላይ እንዲበር ይለቀዋል።


አሮንም በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጥልባቸዋል፥ አንዱ ዕጣ ለጌታ ሌላው ዕጣ ለዐዛዜል ይሆናል።


አሮንም ለጌታ ይሆን ዘንድ ዕጣው የወደቀበትን ፍየል ያቀርባል፥ ስለ ኃጢአትም መሥዋዕት ያደርገዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios