ኢሳይያስ 53:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰማነውን ነገር ማን አምኖአል? የጌታስ ክንድ ለማን ተገልጦአል? አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰማነውን ነገር ማን አምኗል? የእግዚአብሔር ክንድስ ለማን ተገልጧል? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቡም እንዲህ ሲሉ ይመልሳሉ፦ “እኛ የምንናገረውን ማን ያምነናል? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገለጠ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታ ሆይ፥ ነገራችንን ማን ያምነናል? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገልጦአል? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰማነውን ነገር ማን አምኖአል? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገልጦአል? |
የጌታ ክንድ ሆይ! ተነሥ፥ ተነሥ፥ ኃይልንም ልበስ፤ በቀድሞው ወራትና በጥንቱ ዘመን በነበረው ትውልድ እንደ ሆነው ተነሥ። ረዓብን የቈራረጥህ ዘንዶውንም የወጋህ አንተ አይደለህምን?
በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ “የሰማያትና የምድር ጌታ አባት ሆይ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ።
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! የተባረክህ ነህ! በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና።
ዐሥራ ሁለቱንም ወደ እርሱ አቅርቦ እንዲህ አላቸው “እነሆ፥ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፤ ስለ ሰው ልጅም በነቢያት የተጻፈው ሁሉ ይፈጸማል።
ይህም ነቢዩ ኢሳይያስ “ጌታ ሆይ! ማን ምስክርነታችንን አመነ? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገለጠ?” ብሎ የተናገረው ቃል እንዲፈጸም ነው።