እግዚአብሔር መንፈሳቸውን ያነሣሣው የይሁዳና የብንያም የአባቶች አለቆች፥ ካህናቱና ሌዋውያኑም ሁሉ ለመሄድና በኢየሩሳሌም ያለውን የጌታን ቤት ለመሥራት ተዘጋጁ።
ኢሳይያስ 51:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አይሞትም ወደ ጉድጓድም አይወርድም፥ እንጀራም አይጐድልበትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐንገታቸውን የደፉ እስረኞች በፍጥነት ነጻ ይወጣሉ፤ በታሰሩበትም ጕድጓድ ውስጥ አይሞቱም፤ እንጀራ አያጡም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስረኞች በፍጥነት ነጻ ይወጣሉ፤ አይሞቱም፤ ወደ ጥልቁ ጒድጓድም አይወርዱም። የሚበሉትንም እንጀራ አያጡም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዳንሽ በኋላ እንግዲህ አይኖርምና፥ አይዘገይምምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አይሞትም ወደ ጕድጓድም አይወርድም፥ እንጀራም አይጐድልበትም። |
እግዚአብሔር መንፈሳቸውን ያነሣሣው የይሁዳና የብንያም የአባቶች አለቆች፥ ካህናቱና ሌዋውያኑም ሁሉ ለመሄድና በኢየሩሳሌም ያለውን የጌታን ቤት ለመሥራት ተዘጋጁ።
ከባቢሎን ውጡ ከከለዳውያንም ኰብልሉ፤ በእልልታ ድምፅ ተናገሩ፥ ይህንንም ንገሩ እስከ ምድርም ዳርቻ ድረስ አውሩ፦ “ጌታ ባርያውን ያዕቆብን ታድጎታል!” በሉ።
ጌታ ግን እንዲህ ይላል፦ ከአንቺ ጋር የሚጣሉትን እጣላቸዋለሁ፥ ልጆችሽንም አድናለሁና፥ በኃያላን የተማረኩ እንኳን ይወሰዳሉ፥ የጨካኞች ብዝበዛም ቢሆን ያመልጣል።